ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር የተለያየው ተከላካይ ነገ ማረፊያው ይታወቃል።
በአሁኑ ሰዓት ለሊጉ የሁለተኛው ዙር ተሳትፎ ወደ ሀዋሳ ያመሩት ኢትዮ ኤሌክትሪኮች ከአንድ ተጫዋች ጋር መለያየት ችለዋል። ከቅዱስ ጊዮርጊስ ወጣት ቡድን ከተገኘ በኋላ ለትውልድ ሀገሩ ድሬዳዋ ከተማ በመጫወት ከብዙሀኑ የስፖርት ቤተሰብ ጋር መተዋወቅ የቻለው የተከላካይ ስፍራ ተጫዋቹ ሚክያስ ካሳሁን ላለፉት ሦስት አመታት በወጥነት ካገለገለበት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ቀሪ ውል እየቀረው በስምምነት መለያየት ችሏል።
በአሁኑ ሰዓት ከተለያዩ ክለቦች ጋር ንግግር እያደረገ የሚገኘው ተጫዋቹ በነገው ዕለት አመሻሹን አዲሱ ክለቡ እንደሚረጋገጥ ያገኘሁት መረጃ አመላክቷል።



