የጦና ንቦቹ ሦስት ተጫዋቾችን ለቀዋል።
ገና በአመቱ አጋማሽ በአራት አሰልጣኞች የመመራት ዕጣ ፈንታ የገጠመው እና በአሁኑ ሰዓት በአሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ እየሰለጠኑ የሚገኙት በሊጉም ደካማ ጉዞን ያደረጉት ወላይታ ድቻዎች ከታችኛው ቡድኑ አሳድጎት ያለፉትን ሦስት አመታት ቆይታ ያደረገው ግብ ጠባቂው አብነት ይስሀቅ ሴኔጋላዊው ግብ ጠባቂ ከሀዲን ኒዲያዬን መፈረሙን ተከትሎ ከክለቡ ሲለያይ ሌላኛውም የቡድዩ የቢ ቡድን ፍሬ ተከላካዩ አስናቀ አምታታው እና ከነገሌ አርሲ ቡድኑን በያዝነው አመት መቀላቀል የቻለው የመስመር ተከላካዩ ምንተስኖት ተስፋዬም ከክለቡ ጋር የተለያዩ ሦስቱ ተጫዋቾች መሆናቸውን አረጋግጫለሁ።



