የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን የተከላካይ አማካዩ ወደ ስብስቡ ቀላቅሏል።
የ2017 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሻምፒዮኑ የአሰልጣኝ ገብረመድህን ሐይሌው ኢትዮጵያ መድን በሊጉ እስከ አሁን በሰበሰባቸው አስራ ሁለት ነጥቦች 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ የሚገኙ ሲሆን ቡድኑ ያለበትን የስኳድ ጥበት ችግር ለመቅረፍ በነፃ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት የተከላካይ አማካዩ ዳንኤል ደምሱን ወደ ስብሰባቸው መቀላቀል የቻሉ ሲሆን የፌድሬሽኑ የTMS ክፍል ባለሙያ ከግል ጉዳዩዋ ስትመለስ ውሉ በይፋ የሚፀድቅ ይሆናል።
ተማሪ ከነበረበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ሕይወቱን ከጀመረ በኋላ በባህርዳር ከተማ ፣ ወልዲያ ፣ ኢትዮጵያ ቡና ፣ መቐለ 70 እንደርታ ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ወልቂጤ ከተማ እና የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ጨምሮ በሁለት አጋጣሚዎች ለአዳማ ከተማ ከተጫወተ በኋላ ቀጣዩ መዳረሻው መድን ሆኗል።



