መነሻ ገጽ ወላይታ ድቻ የጦና ንቦቹ ቀጣይ አሰልጣኝ ታውቋል
ወላይታ ድቻዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

የጦና ንቦቹ ቀጣይ አሰልጣኝ ታውቋል

አጋራ
አጋራ

በያዝነው የውድድር ዘመን ወላይታ ድቻን የሚመራው ሦስተኛው አሰልጣኝ ታውቋል።

ሀያ ቡድኖችን በሚያሳትፈው የ2018 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ካደረጋቸው አምስት ጨዋታዎች አራቱን ተሸንፎ በአንዱ ነጥብ በመጋራት በደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ ላይ የተቀመጠው ወላይታ ድቻ አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራን ከአራት የሽንፈት ጉዞ በኋላ በማሰናበት ረዳት አሰልጣኙ ቴዎድሮስ ቀነኒን በጊዜያዊ መንበሩ ሾሞ ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር 2ለ2 ከተጠናቀቀው ጨዋታ በኋላ የመስራት ነፃነትን አጣሁ በማለታቸው ከጊዜያዊ አሰልጣኙም ጋር ክለቡ መለያየቱ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ክለቡ አሰልጣኝ ለመቅጠር ሰፋ ያለ ጊዜን ማስፈለጉን በመገንዘብ ከሀዋሳ ከተማ የተስፋ ቡድኖች ጀምሮ እስከ ዋናው ቡድን ድረስ የግብ ጠባቂ እንዲሁም ረዳት አሰልጣኝ በመሆን ጭምር ከአስራ ስድስት አመታት በላይ ያገለገለውን በኋላም በካፋ ቡና በከፍተኛ ሊጉ በማሰልጠን ቆይታን ያደረገው እና በወላይታ ድቻ የአካል ብቃት አሰልጣኝ እያገለገለ የነበረው አሰልጣኝ አምጣቸው ሐይሌ የኤ ላይሰንስ (ሪፍሬሽመንት ኮርስ ይቀረዋል) ባለቤት መሆኑን ተከትሎ በሚያሳየው ውጤት መሠረት ጊዜያዊ የጦና ንቦቹ አሰልጣኝ በመሆን በዓመቱ የክለቡ ሦስተኛው አሰልጣኝ ሆኖ መሾሙን ሀትሪክ ስፖርት አረጋግጧል።

ወላይታ ድቻ የፊታችን ዕርብ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በአዲስ አበባ ስታዲየም በስድስተኛው ሳምንት መርሀ ግብር የሚያስተናግድ ይሆናል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...