ሸገር ከተማ ወደ ዝውውሩ ጠለቅ ብሎ መግባት የቻለ ሲሆን ከ ግብ ጠባቂዋ ሮማን ጋር መስማማታቸውን የገለፅን ሲሆን አመሻሹን ሶስት ተጨማሪ ተጨዋቾች እና የቡድኑን ዋና አሰልጣኝ ውል ማራዘም ችሏል ።
በዛሬው እለት ከድሬዳዋ ቡድኑን የተቀላቀለችው አለሚቱ ድሪባ ስትሆን ወራዊ ደሞዟ ያልተጣራ 151,539.00 ለሁለት ዓመት የሚያቆያትን ውል መፈረም ችላለች።
ሶስተኛ ፈራሚ በመሆን ሸገር ከተማ የደረሰችው የምስራች ሞገስ ስተሆን የምስራች ሞገስ በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በግሏ በድሬዳዋ ከተማ ጥሩ የሚባል እንቅስቃሴ ማድረግ ችላለች ተጨዋቾዋ የአንድ ዓመት ኮንትራት የፈረመች ሲሆን ወራዊ ደሞዝ ያልተጣራ 120,770.00 የሚከፈላት ይሆናል ።
በዛሬው እለት ሌላኛው ሸገር ከተማን የተቀላቀለች ማህሌት ወርቁ ስትሆን በድሬዳዋ ከተማ ዘንድሮ መጫወት ችላለች ማህሌት ከ ሸገር ከተማ ጋር ለ አንድ ዓመት ለመቆየት በ ወር ያልተጣራ 120,770.00 የሚከፈላት ይሆናል።
- ማሰታውቂያ -

በዛሬው ውል ማደስ የቻለው ሸገር ከተማን ለመጀመሪያ ጊዜ በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ እንዲሳተፉ ማድረግ የቻለው አሰልጣኝ ድሪባ ጃምቦ ሲሆን ከዚህ በፊት አዳማ ከተማ እና ንፋስ ስልክ ላፍቶን ማሰልጠን ችሏል አሰልጣኙ በሸገር ከተማ ለሁለት ዓመት የሚያቆየውን አዲስ ውል መፈረም ችሏል ።



