መነሻ ገጽ ቃለመጠይቅ ኳስ ተጫዋች ባልሆን ኪቦርድ እና ድራም እጫወት ነበር። የምፈራው አጥቂ የለም ሮማን አምባዬ
ቃለመጠይቅዜናዎችየኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ

ኳስ ተጫዋች ባልሆን ኪቦርድ እና ድራም እጫወት ነበር። የምፈራው አጥቂ የለም ሮማን አምባዬ

አጋራ
አጋራ

ከኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የተገኘችው የነገ የሉሲዎቹ ተስፋ ሮማን አምባዬ   የሳምንቱ እንግዳችን ናት ተከታተሉን

ሀትሪክ: ሮማን የት ተወለደች የትስ አደገች?

ሮማን : በአርባ ምንጭ ዙርያ ወረዳ ጫኖ ሞሌ ቀበሌ ነው የተወለድኩት እድገቴ አርባ ምንጭ በተለምዶ መናኸሪያ ሰፈር ወይም 04 ቀበሌ ነው !

ሀትሪክ : ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ እንዴት እና በማን አማካኝነት መግባት ቻልሽ?

ሮማን : ፕሮጀክት በምጫወትበት ጊዜ መልማዮቹ መተው ጥሩ እንቅስቃሴ ማድረጌን በመመልከት ልመረጥ ችያለው ።

ሀትሪክ : ዘንድሮ በድሬዳዋ አሪፍ ጊዜን ማሳለፍ ችለሻል መጨረሻ አካባቢ ጉዳት ብታስተናግጂም ከ ድሬ በፊት የት የት መጫዋት ቻልሽ ???

ሮማን : ያው አካዳሚ ተመርቄ ከወጣው በዋላ በ ቦሌ ክፍለ ከተማ መጫወት ቻልኩኝ ከዛ ወደ ድሬዳዋ አቀናው

ሀትሪክ : በእግር ኳስ ህይወትሽ በጣም አስከፊው እና ያስደሰተሽ ጊዜ ?

ሮማን: አስከፊው ጊዜዬ  አካዳሚ 3ኛ ዓመት ሰልጣኝ እያለው  ከ17 ዓመት በታች ናሽናል ቲም ሳልመርጥ የቀረሁበት ጊዜ በጣም  አስከፍቶኛል :  እንደዛው በ ቀጣዩ ዓመት  4ኛ ዓመት ሰልጣኝ ሆኜ
ከ18 ዓመት በታች ናሽናል ቲም የተመረጥኩበት ጊዜ የተሰማኝ ደስታ መገለፅ አልችልም ።

ሀትሪክ : በጣም የምትፈሪያት አጥቂ አለች ካለች ማነች ??

ሮማን : የለም

ሀትሪክ : ለመጀመሪያ ጊዜ ለ ናሽናል ቲም ስትመረጪ የት ነበርሽ የተሰማሽን ስሜት በጥቂቱ አጋሪን

ሮማን : ለመጀመሪያ ጊዜ ስመረጥ ኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ነበርኩኝ የተለየ ስሜት ነበርኝ በጣም ደስ ይላላል ሀገርን ለማገልገል መጠራት !

ሀትሪክ : አብርያት ብጫወት የምትያት ግብ ጠባቂ ?

ሮማን : ታሪኳ በረገና

ሀትሪክ : ግብ ጠባቂ ለመሆን ምን አነሳሳሽ ?

ሮማን: ፖሮጀክት ስጫወት ኮች ፀጋአብ ኢሳያስ
ነበር ሀሳቡን ያመጣልኝ ሞከረኩት የተሻለ ነገር ነበረኝ በዛው ቀጠለኩ !

ሀትሪክ : በሊጉ  ካለፉት ዓመታት ምን ተማርሽ ??

ሮማን :  ገና ብዙ መሰራት እንዳለብኝ እና ሀገሬን ለረዥም ዓመታት በወጥነት ለማገልገል መስራት እንዳለብኝ ።

ሀትሪክ : ኮንትራትሽ ተጠናቋል ከ አንዳንድ ቡድኖች ጋር ስምሽ ተያይዞ እየተነሳ ነው በየትኛው ቡድን እንመለከትሻለን ??

ሮማን : እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ከሸገር ከተማ  ጋር እየጨረስኩ ነው በሸገር ከተማ እከሰታለው !

ሀትሪክ : ሮማን ከስፖርት ውጪ በምን ትዝናናለች ??

ሮማን : ኪቦርድ እና ድራም በመጫወት !

ሀትሪክ : ሀገራችን ምርጥ ከሚባሉ ሴት ተጨዋቾች አንድ ጥሪ ብትባይ ማንን ትጠሪያለሽ ???

ሮማን : ሎዛ አበራ

ሀትሪክ : ባሳለፍየው ሳምንት ”ጀግኒት ”በሚል ቃል የቀድሞ የሉሲዎቹ ተጨዋቾች እና የአሁኖቹ ተጨዋቾች ጨዋታ አድርጋችሁ ነበር ምን ተሰማሽ በጨዋታው በመሳታፍሽ ??

ሮማን : በጣም በጣም ደስ ብሎኛል እደል ደርሶኝ ከነሱ ጋር በመጫወቴ በጣም  ደስተኛ ነኝ የነሱን ፈለግ ለመከተልም ቆርጬ ተነስቻለው ።

ሀትሪክ : በክረምት ምን በመስራት እያሳለፍሽ ነው ??

ሮማን : ከልምምድ ውጭ ቸርች ውስጥ በማገልገል እና አንዳንዴ የት/ት ኮርሶችን በመማር !

ሀትሪክ : ሮማን እግር ኳስ ተጨዋች ባትሆን ምን ትሆን ነበር ??

ሮማን : ቸርች ውስጥ ኪቦርድ እና ድራም በመጫወት አገለግላለው እና አገልጋይ እሆን ነበር

ሀትሪክ : ወደ አስገዳጅ ጥያቄ ልውሰድሽ :- ከ ሎዛ አበራ እና  ከ ረሂማ

: ከ ሴናፍ ዋቁማ እና  አረጋሽ ካልሳ
:ከሰናይት ቦጋለ እና ብርቱካን ገ/ክርስቶስ   አንድ ብቻ ነው መጥቀስ ሚቻለው

ሮማን : አለመመለስ ብቻል ደስ ይለኛል ግን በጣም ነው ምውዳቸው በጣም ነው ማከብራቸው የኢትዮጱያ እንቁ ናቸው ግን ሎዛ አበራ አረጋሽ ካልሳ ሰናይት ቦጋለ

ሀትሪክ : በመጨረሻ ቀረ የምትይው ወይም ማመስገን ምትፈልጊው ካል እድሉን ልስጥሽ !

ሮማን : በመጀመርያ ለዚህ ሁሉ ነገር እንዲደርስ አቅም ጉልበት ለሆነለኝ ለልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ለርሱ ይሁንለት። በመቀጠል አብዝቼ እምወዳቸው ቤተሰቦቼ እናቴንና አባቴን ለዚህ ክበር እንድደርስ በፀሎትም በተለያዩ ሀሳቦችና ምክር ከጎኔ ለነበሩ ወዳጅ ዘመዶቼ ከፕሮጀክት ጀምሮ አሁን ላለውበት ደረጃ እንዲህ ደርስ ያሰለጠናቸኝ ላገዛቸኝ ኮቾች ለደጋፍዋቸ ምስጋናዬ ላቅ ያለ ነው እንዲሁም በጣም እምወዳቸሁ ማከብራቸሁ የልብ ጓደኞቸን እነዲሁም ሎዞ አበራ እና ባለቤቷ ዮሐንስ ፍቃድ (Jhon) ከልብ ላመሰግናቸው እወዳለው አመሰግናለው።

ሀትሪክ :ጊዜሽን ሰተሽን አብረሽን ስለቆየሽ ከልብ እናመሰግናል ። እንግዲ ከ አዲሱ ቡድንሽ ጋር መልካም የውድድር ጊዜ ተመኘንልሽ

ሮማን : እኔም እኔን መርጣችሁ ቃለመጠይቅ ስላደረጋችሁኝ አመሰግናለሁ !

የሳምንት እንግዳ ፕሮግራማችንን በዚህ ቋጨን በቀጣይ በሌላ እንግዳ እንመለሳለን መልካም ሳምንት !

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የ32ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አህመድ ረሺድ (ድሬደዋ ከተማ) : በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀምራዊ ለባሾቹ እና የጣና ሞገዶቹ ጣፋጭ ሦስት ነጥብን ወደ ቋታቸው ከተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ባህርዳር ከተማ ወሳኝ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና ሲሸነፍ በተጠባቂው ጨዋታ መቻል በጎል ፌሽታ ነገሌን ረቷል

በሳምንቱ የመጀመሪያ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በሀድያ ሆሳዕና ሽንፈት ሲያስተናግድ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

ውጤት ለውጧል የተባለው ዳኛ ተባረረ

በዮሴፍ ከፈለኝ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውጤት ለውጠዋል የተባሉ አርቢትሮችን ወደመጡበት መመለሱን አሁንም ቀጥሏል። ከቀናት...