በአሰልጣኝ ግርማ ታደሰ እየተመራ ለቀጣዩ የውድድር አመት ተጠናክሮ ለመቅረብ እስከአሁን የነባር ተጫዋቾቹን ውል እያደሰ እና እዮብ አለማየሁን እንዲሁም በረከት ወንድሙን የመሳሰሉ ተጫዋቾች ማስፈረም የቻለዉ ሀድያ ሆሳዕና አሁን ደግሞ ተጨማሪ ተጫዋች ማስፈረሙ ታውቋል።
በዚህም ከወልቂጤ ከተማ ከለቀቀ በኋላ ያለፉትን ሁለት የውድድር አመታት በመዲናዉ ክለብ ኢትዮጵያ ቡና ማሳለፍ ችሎ የነበረዉን የፊት መስመር ተጫዋች ጫላ ተሽታ ወደ ስብብስባቸዉ መቀላቀላቸው ታውቋል። ተጫዋቹም በነብሮቹ ቤት የሁለት አመት የኮንትራት ውል የሚፈርም ይሆናል።