በአሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የሚመሩት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ተጨማሪ ተጫዋቾችን ከአርባምንጭ ከተማ አስፈረሙ።
እንዳልካቸው መስፍን አዲሱ የኤሌክትሪክ ተጫዋች ሆኗል። የቀድሞው የጋሞ ጨንቻ እና ያለፉትን አራት አመታት በአርባምንጭ ከተማ ያሳለፈው አማካዩ ቀጣይ መዳሻው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሆኗል።
ሌላኛው ፈራሚ አሸናፊ ተገኝ ሆኗል። እንደ እንዳልካቸው ሁሉ በአርባምንጭ ከተማ አራት አመታትን ያሳለፈው የቀድሞው የጋሞ ጨንቻ የመስመር አጥቂ ማረፊያው ኤሌክትሪክ ሆኗል።
አስተያየት ይስጡ