አሰልጣኝ ገብረመድህን ሐይሌ ረዳቶቻቸው ታውቀዋል
ኢትዮጵያ ቡናን በሁለት አመት ውል የተቀላቀሉት አሰልጣኝ ገብረመድኅን ሐይሌ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኙ ሲሆን በዛሬው ዕለት ደግሞ ረዳቶቻቸው ታውቀዋል። አሰልጣኙ የቀድሞው የመቐለ ዩኒቨርስቲ መምህሩ እና በኢትዮጵያ መድን የአሰልጣኙ ረዳት የነበሩት ዶ/ር ለይኩን ታደሰ ረዳት አሰልጣኛቸው ሲሆን የቀድሞው የድሬዳዋ እና ኤሌክትሪክ አንጋፋ ግብ ጠባቂ ከአሰልጣኙም ጋር ለተከታታይ ሦስት አመታት በመድን ቤት የግብ ጠባቂ አሰልጣኝ ሆኖ ያገለገለው አምባዬ በፍቃዱ የአሰልጣኝ ገብረመድኅን ረዳት ሆነው በዛሬው ዕለት ተሹመዋል።
አስተያየት ይስጡ