አዲስ አዳጊዎቹ ወደ ዝውውሩ ገብተዋል።
በአሰልጣኝ ማቲዮስ ለማ የሚመሩት አዲስ አዳጊዎቹ ጋሞ ጨንቻዎች ከከፍተኛ ሊጉ ሁለት አዳዲስ ተጫዋቾችን ሲያስፈርሙ የስምንት ነባሮችን ውል አራዝመዋል።
ክለቡን የተቀላቀሉት አዳዲሶቹ ተጫዋቾች በቤንች ማጂ እና ሀረር ሲቲ የሚታወቀው አጥቂው መሐመድ ናስር እና የባቱ ከተማው አማካይ ሳሙኤል ጃጊሶ ናቸው።
ክለቡ ከአዳዲሶቹ በተጨማሪ የተከላካዩ አኮ ቦቃ ፣ መኮንን መና ፣ ዘካሪያስ ጆብር እና ብሩክ ሳካሌ የአማካዩቹ ጌታሁን ገዛኸኝ ፣ የትምጌታ ታደሰ ፣ ብሩክ ጥላሁን እና የአጥቂው ዘካሪያስ ተክሌን ውል ለተጨማሪ አመት አራዝሟል።
አስተያየት ይስጡ