ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አማካዩን ሲያስፈርም የአራት ነባሮችን ውል ደግሞ አደሰ።
በአሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ የሚመሩት ኢትዮጵያ ንግድ ባንኮች የመጀመሪያ ፈራሚያቸው አማካዩ ሙሉቀን አዲሱን ሲያደርጉ የአራት ነባሮችን ውል ደግሞ አደሰ።

የቀድሞው የገላን ከተማ ፣ አዲስ አበባ ከተማ ፣ ሲዳማ ቡና እና ያለፉትን ሁለት አመታት ደግሞ በወላይታ ድቻ ቤት የቆየው አማካዩ ማረፊያው የቀድሞው አሰልጣኙን ጥሪ ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሆኗል።
ክለቡ ከሙሉቀን በተጨማሪ የተከላካዩ አቤኔዜር ተክሉ ፣ የአማካዩ ብሩክ ብፁዕአምላክ ፣አማካይ ዮሐንስ ኪዳኔ እና የግብ ጠባቂው አማኑኤል ደስታን ውል ደግሞ አራዝሟል።
አስተያየት ይስጡ