ባለ ድንቅ ብቃቱ ተጫዋች ሱራፌል ዳኛቸው ወደ ሎደን ዩናይትድ ካመራ በኋላ ከልምምድ ውጪ በጨዋታ ላይ ሲሰለፍ አልታየም።
ሎደን ዩናይትድ ሳምንታት በኋላ በሚጀምረው የ”USL CHAMPIONSHIP” የሚጫዋቱ የክለቡን ተጫዋቾች የማልያ ቁጥር ይፋ ሲያደርግ ሱራፌል ዳኛቸውም ተካቷል።
ክለቡ ይፋ እንዳደረገው ከሆነም ሱራፌል ዳኛቸው በቡድኑ 19 ቁጥር ማልያን የሚለብስ ይሆናል።
ይህም ከ11 ሳምንታት በኋላ በሚጀምረው የ”USL CHAMPIONSHIP” ላይ ተጫዋቹ ወደ ጨዋታ እንደሚመለስ ፍንጭ የሰጠ ሆኗል።

እስከ 2026 ድረስ ከክለቡ ጋር ውል ያሰረው ሱራፌል በወረቀት ጉዳዮች አለመጠናቀቅ ምክንያት እ.አ.አ በ2024 የውድድር ዘመን ለክለቡ ጨዋታ አለማድረጉ ይታወቃል።
አስተያየት ይስጡ