የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
በረከት ወልዴ (ቅዱስ ጊዮርጊስ) በኢትዮጵያ ዋንጫ ውድድር 1 እንዲሁም ከታች በተጠቀሱት 4 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ ካርድ ተመልክቷል ።
ቅዱስ ጊዮርጊስ – ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲ
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
ቅዱስ ጊዮርጊስ – ኢትዮ ኤሌትሪክ
- ማሰታውቂያ -

አዳማ ከተማ – ቅዱስ ጊዮርጊስ
በመሆኑም ተጫዋቹ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ በተጨማሪ የገንዘብ ቅጣት ብር 1500 እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል ።
ስሁል ሽረ ክለቡ ከመቻል ጋር ባደረገው የ13 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የስሁል ሽረ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ነፃነት ገብረመድህን
- ጎይቶም ነጋ
- ዊሊያም ሰለሞን
- አሰጋኸኝ ጴጥሮስ
- ክፍሎም ገ/ሂወት
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ እፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
ሲዳማ ቡና ክለቡ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ባደረገው የ13 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሲዳማ ቡና ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ፍራወል መንግስቱ
- ያሬድ ባየህ
- ሐብታሙ ታደሰ
- ደስታ ደሙ
- ኢማኑኤል ሳባን ላሪዬ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
ሀዲያ ሆሳዕና ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው የ13 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የሀዲያ ሆሳዕና ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ሰመረ ሀፍተይ
- ደስታ ዋሚሾ
- በረከት ወልደዮሐንስ
- ብሩክ ማርቆስ
- ሄኖክ አርፊጮ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
ፋሲል ከነማ ክለቡ ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ባደረገው የ13 ኛ ሳምንት እግርኳስ ጨዋታ የፋሲል ከነማ ቡድን ተጫዋች የሆኑት
- ተመስገን ካስትሮ
- ሐብታሙ ተከስተ
- ማርቲን ኪዛ
- ብሩክ አማኑአል
- መንገሻ አየሩ
በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል የ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ወስኗል፡፡
አቶ መንግስቱ ታደሰ /ኢትዮጵያ ቡና የክለብ-አመራር/ ኢትዮጵያ ቡና ከድሬዳዋ ከተማ ጋር በነበረው የ12ኛ ሳምንት ግጥሚያ ጨዋታው ከተጠናቀቀ በኋላ
የእለቱ ዳኞችን አጸያፊ ስድብ ስለመሳደባቸው ሪፖርት ቀርቦባቸዋል ። ስለሆነም አመራሩ ለፈጸሙት ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ ክፍል 3 ምዕራፍ 3 አንቀፅ 66 በተቁ 1 መሠረት ከ14ኛ ሳምንት ጀምሮ ኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጋቸውን 6/ስድስት/ ተከታታይ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ወደ ስታድየም ገብተው እንዳይመለከቱ እንዲታገዱ/ በተጨማሪም ብር 5 000 /አምስት ሺህ / እንዲከፍሉ የውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ ወስኗል።


