የውድድር ዓመቱን በኢትዮጵያ መድኅን በማሳለፍ ላይ የነበረው ጋቶች ፓኖም ወደ ኢራቅ ማምራቱ እርግጥ ሆኗል።
ግዙፉ ተጫዋች ኒውሮዝ ስፖርት ክለብን የተቀላቀለ ሲሆን በክለቡም የአንድ አመት ውል ተፈራርሟል።
1.90 ሜ የሚረዝመው ጋቶች ከዚህ ቀደም ከሀገር ውጪ በሩስያ ፣ በግብፅ እና በሳዑዲ አረቢያ ክለቦች ማሳለፉ ይታወቃል።
ከተመሰረተ የ31 ዓመት ዕድሜ ያለው ኒውሮዝ ስፖርት ክለብ በውድድር ዘመኑ ካደረጋቸው 13 ጨዋታዎች በ4 አሸንፎ ፣ በ2 አቻ ሲለያይ በቀሪ 7 ሽንፈት አስተናግዷል።
- ማሰታውቂያ -
20 ክለቦች ባሉበት ሊግም በ14 ነጥቦች 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።



