ቅዱስ ጊዮርጊስ የወዳጅነት ጨዋታ ዛሬ ያካሂዳል !

በደብረዘይት ልምምዳቸውን ከ ሳምንታት በፊት የጀመሩት ፈረሰኞቹ ከ ዴቪድ ማሂር ስንብት በኋላ በአዲሱ አሰልጣኝ ፍራንክ ናቶል ስር በዛሬው እለት የአቋም መፈተሻ እንደሚያደርግ ለማወቅ ተችሏል ።

ፈረሰኞቹ ተለዋጭ ነገር ከሌለ በቀር ዛሬ ረፋድ 4:00 ሰዓት ላይ ከ አዳማ ከተማ ጋር በ ደብረዘይት የክለቡ የልምምድ ስፍራ ጨዋታቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል ።

የፈረሰኞቹ ተጋጣሚ አዳማ ከተማዎች ከዚህ የወዳጅነት ጨዋታ በኋላ በነገው ዕለት ጨዋታው ወደ ሚካሄድባት ድሬደዋ ከተማ ይጓዛሉ ።

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በድሬደዋ ቆይታቸው በሳምራ ሆቴል እንደሚያርፉ ለማወቅ ተችሏል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor