ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአሰልጣኙ ጋር ተለያየ

ደቡብ አፍሪካዊው አሰልጣኝ ማሂር ዴቪስና ፈረሰኞቹ በስምምነት ተለያዩ።

ዛሬ በተሰማ መረጃ አሰልጣኙና ክለቡ በስምምነት መለያየታቸውና ለጊዜውም ቢሆን ከቀናት በፊት ወደ ቡድኑ የተመለሰው አሰልጣኝ ዘሪሁን ሸንገታ የአሰልጣኝነት ሚና እንደሚወስድ የቡድን መሪው አቶ ታፈሰ በቀለ ገልጸዋል።

ከቅጣት መልስ ሳላህዲን ሰይድ ቡድኑን ሲቀላቀል ምክትል አሰልጣኝ የነበረው ደረጄ ተስፋዬ ወደ ተስፋ ቡድን እንዲመለስ ተደርጓል ተብሏል። አሰልጣኙ ቅዱስ ጊዮርጊስን ይዘው 15 ጨዋታ አድርገው 7 ጊዜ ሲረቱ 5 ጊዜ አቻ ወጥተው 3 ጊዜ ተረተው በ26 ነጥብና 9 ግብ 3ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport