የዋልያዎቹ ጨዋታ የታዳሚያንን ቁጥር ካፍ አሳወቀ !

ካፍ ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መረጃ በዚህ ሳምንት በሚካሄዱ የ አህጉሪቱ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች ላይ የደጋፊዎችን ቁጥር ወስኗል ።

በዚህም መሰረት በነገው ዕለት ዋልያዎቹ ከ ማዳጋስካር ጋር በሚያካሂዱት ተጠባቂ መርሀ ግብር ላይ ካፍ ጨዋታው ያለ ደጋፊ በዝግ እንዲካሄድ ውሳኔ ሲያስተላልፍ ሁለት መቶ ቪአይፒ እንግዶች እንዲታደሙ ፍቃድን አግኝቷል ።

በተቃራኒው የማዳጋስካር ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ከ ኒጀር ጋር የሚያካሂዱት መርሐ ግብር 1,500 ደጋፊዎች ብቻ እንዲታደሙበት ካፍ ፈቃድ ሰጥቷል ።

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor