መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኙን እያስተዋወቀ ነው
ቅዱስ ጊዮርጊስቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎች

ቅዱስ ጊዮርጊስ አሰልጣኙን እያስተዋወቀ ነው

አጋራ
አጋራ

ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲሱን አሰልጣኙን ሰርቪያዊው ዝላታንኮ
ክራምፖቲችን መቅጠሩን ይፋ አድርጓል።
ጠመንቻ ያዥ በሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ የስፖርት ማህበር ጽ/ቤት እየተሰጠ ባለው መግለጫ ላይ ባለፉት 8 ወራት ለሀላፊነቱ በርካታ አሰልጣኞች ሲያወዳድር ቆይቶ አሰልጣኙን ከመረጠ አንድ ወር እንዳለፈው ክለቡ አስታውቋል።

አሰልጣኙ ሳይመርጥ ክለቡ ተጨዋቾችን አምጥቶ ለአሰልጣኝ መስጠት ላይ የምላሽ የሰጡት የቦርድ ፕሬዝዳንቱ አቶ አብነት ገብረ መስቀል “ለሹራቡ ፍቅር ያላቸው ለክለቡ የሚለፉና ክለቡን የሚወዱ ተጨዋቾቻችን ይመርጡልናል ተጨዋች ለመመልመል ያልዞርነው ያሉትም ይታወቃሉ ማሊያ የሚቀይሩትኮ እነሱው ናቸው እንደ አሸን የፈላ ወጣት የለም መርጠን ለነገ ብለን የምናስባቸው ታዳጊዎች የሉም ወደፊት ግን አሰራራችን ይቀየራል በርግጥም አመራረጣችንም ችግር የለውም ትክክለኛ ነው ብዬ አላምንም በቀጣይ ሊጉ ሲያድግ ሲቀየር እኛም እንቀየራለን” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።
አቶ አብነት “እኛ ያቀረብነውን መመዘኛ ያሟሉ አሰልጣኞች የሉም በርትተው ጥሩ ሆነው ከተገኙ በሀገራችን አሰልጣኞች መሰልጠን አንጠላም” ሲሉ መልሰዋል።

አሰልጣኙ ዝላታንኮ ክራምፖቲች በበኩላቸው “አፍሪካ ውስጥ መስራት ከባድ ከክፍያም ሆነ ከተመቸ ሁኔታ አንጻር ከባድ ነው የመጨረሻ ጨዋታዬ ያንግ አፍሪካ ይዤ 5 ጨዋታ አደረኩ 4 ድል 1 አቻ ወጣሁ ያም ሆኖ እዚህ መግለጽ የማልፈልገው ትልቅ ችግር አለ በቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ይገጥመኛል ብዬ አላስብም። ስለ እግር ኳስ ፍልስፍናም ማውራት አልፈልግም ቃል የምገባው በጊዮርጊስ ተጨዋቾች በኩል በታክቲክ የበሰለና በዲሲፕሊን የታነጸ ቡድን እንደምገነባ ነው ” ብለዋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

ገዛኸኝ ደሳለኝ (ሸገር ከተማ) : ክለቡ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ባደረገው የ26ኛ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና በዝናባማው ጨዋታ በመቻል ሲረታ የጣናው ሞገድም አሸንፏል

እጅግ በከባድ ዝናብ ታጅቦ በተደረገው ጨዋታ መቻል የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 3ለ1...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...