መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቅዱስ ጊዮርጊስ አራት ተጫዋቾችን የስብስቡ አካል ሲያደርግ የአማካዩ መፈረም አጠራጥሯል
ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዝውውር ዜናዎች

ቅዱስ ጊዮርጊስ አራት ተጫዋቾችን የስብስቡ አካል ሲያደርግ የአማካዩ መፈረም አጠራጥሯል

አጋራ
አጋራ

በሰርቪያዊው አሰልጣኝ ጥቆማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ዝውውር ገብቷል።

በቀጣዩ የውድድር ዘመን ሰርቪያዊውን አሰልጣኝ ሰርዲ ሚሊት ሚቾን በዋና አሰልጣኝነት ከአመታት በኋላ ለመቅጠር ከጫፍ የደረሰው እና በአሁኑ ሰዓት ግን በአሰልጣኝ ፋሲል ተካልኝ የሚመሩት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከበርካታ ፈተናዎቹ በኋላ ችግሮቹን ከቀረፈ በኋላ በአሁኑ ሰዓት በሰርቪያዊው አሰልጣኝ ትዕዛዝ እና ጥቆማ አራት የውጪ ዜጋ ተጫዋቾችን በዛሬው ዕለት አመሻሽ በሸራተን አዲስ ሆቴል በይፋ ማስፈረሙን ያሳውቃል።

በዚህ አመት ለየትኛውም ክለብ እየተጫወተ ያልነበሠው የ23 አመት ዕድሜ እንዳለው የሚነገርለት እግር ኳስን በሀገሩ ጋና ማውንቴን በኋላም ለአልቫኒያው ስኬን ደርቪው ኮርሲ ፣ ኬ ኤፍ ቲርቡኒ ፣ ኬ ኤፍ ካስቶሮኒ የተጫወተው ኬልቪን ዶሴ እና ለጋናው ስትሮም ሶከር ፣ ለአልባኒያው ስኬንደርቪው ኮርሲ ፣ ፓርቲዛኒ ፣ ኬ ኤፍ ፕላዚያ ፣ ኬ ኤፍ ቲራን እና ለኮሶቮው ባልካኒ በመሐል አጥቂ የተጫወተው የ26 አመቱ አልፍሬድ ሜንሳህ ለክለቡ በአንድ አመት ውል የፈረሙ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን በደቡብ አፍሪካ ሊግ የተጫወቱ ሌላ ሁለት ቀሪ ተጫዋቾችም ለክለቡ አመሻሽ እንደሚፈርሙ ታውቋል።

ከክለቡ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ ልምምድ ሲሰራ የነበረው አማካዩ ፉአድ ፈረጃ በአሁኑ ሰዓት በክለቡ ካምፕ የማይገኝ ሲሆን ለክለቡ የመፈረሙም ነገር አጠራጣሪ እንደሆነ ያገኘሁት መረጃ ጠቁሟል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...