በሳምንቱ የማሳረጊያ ቀን በተደረገ ጨዋታ ነገሌ አርሲ ወደ ሊጉ መሪ የቀረበበትን ድል ሲያሳካ ኢትዮጵያ መድንም አሸንፏል።

የመዲናይቱን ክለቦች ኢትዮጵያ መድን እና ነገሌ አርሲ የተገናኙበት ጨዋታ በመድን የበላይነት ተደምድሟል። 56ኛው ደቂቃ ላይ ከብሩክ አውላቸው መነሻ ሆና ብሩክ ሙሉጌታ በጥሩ ሁኔታ ያሾለከለትን ኳስ ወጣቱ አማካይ ዳዊት አውላቸው ወደ ጎልነት ቀይሮ መድኖችን ቀዳሚ አድርጓል። ጨዋታው ቀጥሎ 70ኛው ደቂቃ ላይ ከቀኝ ተነስታ ዘላለም አበበ ከሳጥኑ ጠርዝ ወደ ውስጥ የጣለውን ኳስ የመድኑ አማካይ አብዱ መሐመድ በግንባር ገጭቶ በራሱ መረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል። 82ኛው ደቂቃ ላይ የመድኑ የግራ ተከላካይ ያሬድ ካሳዬ ሳጥን ውስጥ ያገኛትን ኳስ ወደ ግብ ሲመታ አብዱላዩ ዲያካም በእጅ ኳስን ነክቷል በሚል የዕለቱ ዳኛ ሚካኤል ጣዕመ የሰጡትን የፍፁም ቅጣት ምት ረመዳን የሱፍ ወደ ጎልነት ለውጦ ኢትዮጵያ መድኖች 2ለ1 አሸናፊ ሆነዋል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሜዳ ላይ የተደረገው ጨዋታ ነገሌ አርሲ 3ለ0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ሊጉ መሪ በይበልጥ ሲቀርብ ድሬዳዋ ከተማ በበኩሉ ወደ ቅርቃር ውስጥ በይበልጥ የገባበትን አጋጣሚ ፈጥሯል። 18ኛው ደቂቃ ላይ ገብረመስቀል ዱባለ ላይ የድሬዳዋ ከተማው የግብ ዘብ አብዩ ካሳዬ በሳጥን ውስጥ በሰራበት ጥፋት የተገኘችን የፍፁም ቅጣት ምት ዳዊት ተፈራ በቀላሉ ዘደ ግብነት ለውጦ ሰጎኖቹን መሪ ማድረግ ችሏል። የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ ሲቃረብ በተሰጠው ጭማሪ 45+3 ላይ ዳዊት ተፈራ ከማዕዘን አሻምቶ ተነካክታ የመጣችለትን ኳስ ዳዊት መለሠ አስቆጥሮ ነገሌዎች 2ለ0 መምራት ችለዋል።

ከዕለታዊ መልስ ከቆሙበት የቀጠሉት ነገሌ አርሲዎች 61ኛው ደቂቃ በፈጣን ሽግግር ኪቲካ ጀማ ከቀኝ ያቀበለውን ተቀይሮ የገባው ከቤ ብዙነህ በጥሩ አጨራረስ ጎል አስቆጥሮ ነገሌ አርሲ 3ለ0 አሸንፏል።
አስተያየት ይስጡ