መነሻ ገጽ ዜናዎች የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

የሊጉ መሪ ሽንፈት ሲገጥመው በድንጉዛ ደርቢ የጦና ንቦቹ እና ኤሌክትሪክ ድል ቀንቷቸዋል

አጋራ
አጋራ

በሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሽንፈትን በሸገር ሲያስተናግድ በጎረቤታሞቹ ደርቢ ወላይታ ድቻ አርባምንጭን ኢትዮ ኤሌክትሪክ ደግሞ ፋሲል ከነማን ሲያሸንፉ የወልዋሎ እና ባህርዳር ጨዋታ ደግሞ ያለ ጎል ተጠናቋል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም ቀዳሚ በነበረው ጨዋታ ሸገር ከተማ የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን 1ለ0 በማሸነፍ ቡናማዎቹ ተከታታይ ሽንፈትን ቀምሰዋል። 32ኛው ደቂቃ ዮሴፍ ታረቀኝ ያሻገራት እና ቢኒያም ፍቅሬ በግንባር ገጭቶ ከመረብ ያሳረፋት ብቸኛ ጎል ቡድኑን አሸናፊ ያደረገችዋ አጋጣሚ ሆናለች።

ሌላኛው በአዲስ አበባ ስታዲየም አምስት ጎሎች የተቆጠሩበት የድንጉዛ ደርቢ ወላይታ ድቻ አርባምንጭ ከተማን 3ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል። እጅግ ጠንካራ ፉክክር ለታየበት ጨዋታ 14ኛው ደቂቃ ከኋላ ክፍሉ የተቀበለውን ኳስ ቴዎድሮስ ታፈሠ ሰንጥቆ ሰጥቶ መሳይ ሠለሞን በድንቅ አጨራረስ ቡድን መሪ ማድረግ ሲችል ከዕረፍት መልስም ከቆሙበት የቀጠሉት ድቻዎች 61ኛው ደቂቃ የአርባምንጩ ቶጓዊ የግብ ዘብ እድሪሱ ኦጎዶጆ በተሳሳተ መልኩ ለተቃራኒው ተጫዋች ለሙሉቀን አዲሱ አቀብሎት እጅግ አስደናቂ ጎልን ከመሐል ሜዳው ጨረር ላይ የግብ ዘቡን መውጣት ተመልክቶ አማካዩ ሁለተኛ ጎል ከመረብ ሲያሳርፍ 70ኛው ደቂቃ ላይ መሳይ ሠለሞን ከሳጥን ውጪ እጅግ ሌላ ግሩም ሦስተኛ ጎልን ለራሱ ደግሞ ሁለተኛ ጎልን መረቡ ላይ አሳርፏል።

የጨዋታውን የመጨረሻ አስር ደቂቃዎች በተሻለ ለመንቀሳቀስ የሞከሩት አዞዎቹ 81ኛው ደቂቃ ከቀኝ የሳጥኑ ክፍል ጋናዊው አጥቂ አብዱራህማን መሐመድ 90ኛው ደቂቃ የግል ጥረቱን ተጠቅሞ ናይጄሪያዊው አጥቂ ፊሊፕ አጃህ ጎል ቢያስቆጥሩም አርባምንጭን ከሸንፈት መታደግ ሳይችሉ የድንጉዛው ደርቢ በወላይታ ድቻ 3ለ2 አሸናፊነት ተጠናቋል።

በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሜዳ ላይ ወልዋሎን ከባህርዳር ከተማ ያገናኘው ጨዋታ ያለ ጎል ሲቋጭ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ግን ፋሲል ከነማን 3ለ1ረቷል። ከዕረፍት መልስ 59ኛው ደቂቃ ቤዛ መድህን ምኞች ደበበን ጫና ውስጥ ከቶ የተቀበለውን ኳስ ከመረብ አሳርፎ ኤሌክትሪክ ቀዳሚ ማድረግ ሲችል 84ኛው ደቂቃ ላይ እዮብ አለማየሁ ሳጥን የደረሰውን ኳስ ወደ ጎል ሞክሮ ካሜሮናዊው ግብ ጠባቂ ሞይስ ፓዎቴ ሲመልሰው አሸናፊ ጥሩነህ ሁለተኛ ጎል ሲያደርገው 88ኛው ደቂቃ ሙከረም ረሺድ ሌላ አስደናቂ ሦስተኛ ጎል አስገኝቷል። በረከት ግዛው በበኩሉ ከሽንፈት ያላዳነች ብቸኛ ጎል ለፋሲል አስቆጥሮ ጨዋታው 3ለ1 በኤሌክትሪክ አሸናፊነት ተጠናቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...