መነሻ ገጽ ወልዋሎ የወልዋሎ ተጫዋቾች ልምምድ አቁመዋል
ወልዋሎዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የወልዋሎ ተጫዋቾች ልምምድ አቁመዋል

አጋራ
አጋራ

በአሰልጣኝ ግርማ ታደሠ የሚመሩት ወልዋሎዎች ልምምድ መስራትን አቁመዋል።

በተጫዋቾች የደመወዝ አለመክፈል ጉዳይ ተደጋግሞ ስሙ የሚነሳው ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ከባህርዳር ከተማ ጋር ያለ ጎል ባለፈው ዕሁድ ካጠናቀቀው የሊጉ የ31ኛ ሳምንት መርሀግብር በኋላ ልምምድ መስራትን አቁመዋል። በያዝነውም አመት ልክ ከዚህ ቀደም እንደነበረው ሁሉ በተመሳሳይ ተግባር ስማቸው ይነሳ የነበረው ቢጫዎቹ ያለፉትን አራት ወራት የደመወዝ ክፍያን ባለ መፈፀማቸው ተጫዋቾቹ በተደጋጋሚ እንዲከፈላቸው ሲያነሱ የነበሩትን ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘታቸው ከትላንት ጀምሮ ልምምድ መስራትን ማቆማቸውን ያገኘሁት መረጃ ያመላክታል።

በኢትዮጵያ ዋንጫ የግማሽ ተፈላሚ መሆን የቻሉት እና በፕሪምየር ሊጉ ደግሞ ለከርሞ ለመሰንበት ብርቱ ትግል እያደረጉ የሚገኙት ወልዋሎዎች ከደመወዝ ክፍያ በተጨማሪ ከሆቴል ዕዳም ጋር ስማቸው እየተነሳ እንዳለም የመረጃ ምንጮቼ በዝርዝር አስረድተውኛል።

በ32ኛ ሳምንት የሊግ ጨዋታውን ከኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር የፊታችን ግንቦት 7 ለማድረግ መርሀግብር የወጣለት ሲሆን ችግሩ ተፈቶ ጨዋታውን ያደርጋል አልያም ምን የተለየ ነገር ሊኖር ይችላል የሚለው ጉዳይ በቀጣይ ይጠበቃል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...