ያለፉትን ሁለት ያክል አመታት በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ የነበረዉ እና ከክለቡ ጋር የሊጉን ዋንጫ ማሳካት ችሎ የነበረዉ ቢኒያም በላይ በመጨረሻም ከክለቡ ጋር መለያየቱ ታውቋል።
በ2009 መጨረሻ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በመልቀቅ ወደ ጀርመን አምርቶ የሙከራ ጊዜን ማሳለፍ ችሎ የነበረዉ እና ወደ አልባኒያዊው ክለብ ስከንደርቡ በማምራት ከክለቡ ጋር የሊጉን የዋንጫ ክብር ማሳካት ችሎ የነበረዉ ፤ በመቀጠል ወደ ስዊዲን በማቅናት ለስሪያንስካ እና ኡሚያ ክለቦች ተጫዉቶ ወደ ሀገር ቤት በመመለስ ለሲዳማ ቡና ፣ መቻል እና ያለፉትን ሁለት ያክል አመታት ደግሞ በፈረሰኞቹ ቤት ቆይታ ማድረግ የቻለዉ የመስመር ተጫዋቹ ቢኒያም በላይ በመጨረሻም ከክለቡ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር መለያየቱን አስታውቋል።
በይፋ ከክለቡ ጋር መለያየቱን በማህበራዊ ትስስር ገፁ ላይ ያሰፈረዉ ቢኒያም በቀጣይ ቀናት ቀጣይ ማረፊያዉ ይታወቃል ተብሎ ሲጠበቅ ፤ ፋሲል ከነማ እና የቀድሞ ክለቦቹ መቻል እንዲሁም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተጫዋቹን ፊርማ ለማግኘት ንግግር ላይ መሆናቸዉም ታውቋል።



