መነሻ ገጽ ቅዱስ ጊዮርጊስ የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አመራሮች ከሀላፊነት ለመነሳት ፍቃደኛ ሆኑ
ቅዱስ ጊዮርጊስዜናዎች

የቅዱስ ጊዮርጊስ የቦርድ አመራሮች ከሀላፊነት ለመነሳት ፍቃደኛ ሆኑ

አጋራ
አጋራ

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽነ ፕሬዚዳንት እና ሌሎች ይመለከተናል ያሉ አካላት ዛሬ ባደረጉት ስብሰባ ቅዱስ ጊዮርጊስ እፎይ የሚልበት ውሳኔ ተወስኗል።

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ ስሙ ከፍ ብሎ የተቀመጠው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከገጠመው አስከፊ የፋይናንስ እና የአስተዳደር ቀውስ የተነሳ ለችግር መዳረጉ ይታወሳል። ክለቡ በዚህ ችግር ውስጥ እያለ ከረጅም አመታት በኋላ ምርጫን በማድረግ የቦርድ አመራሮችን መምረጥ የቻለ ሲሆን በዚህ ጉዳይ ደስተኛ ያልሆኑ አካላትም ወደ ህግ በማምራት ክስ ሊመሠረቱ ችለዋል። በዚህ ሁሉ ጉዳዮች ውስጥ ግን ከሜዳ ውጪም ሆነ ሜዳ ላይ አቅም እየከዳው የመጣውን አንጋፋውን ክለብ በህይወት ለማቆየት እና ወደቀደመ ክብሩም እንዲመለስ ሲደረግ የነበሩ ጥረቶች ዛሬ መፍትሄ ያገኘ ይመስላል።

የክለቡ የቦርድ አመራር ሆነው የተመረጡት እና በተደጋጋሚ ተቃውሞን ያስተናገደው የአቶ አብነት ገብረመስቀል አመራር ከቦታው ለመነሳት ፍቃደኛ መሆን የቻለ ሲሆን ክለቡን በፍጥነት ወደዝናው እና ችግሮቹም እንዲፈቱ አስር ገለልተኛ የሆነ ኮሚቴ መመረጥ የቻለ ሲሆን በቦርዱም ላይ ክስ መስርተው የነበሩ አካላትም ክሱን ለማንሳት ፍቃደኛ መሆን እንደቻሉ ታውቋል። ይህ ጉዳይ መስመር መያዝ እንዲችልም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ ፣ የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ አዲሱ ሀላፊ አቶ አሰግደው ሀይለጊዮርጊስ እና የአዲስ አበባ ከተማ እግር ኳስ ፌድሬሽን ፕሬዝዳንት ኢንጅነር ሀይለየሱስ ፍሰሀ ትልቁን ሚና መወጣታቸውም ተሰምቷል።

ከቀጣዩ ሳምንት የመጀመሪያዎቹ ቀናት አንስቶ አዲሱ ጊዜያዊ ተመራጭ ኮሚቴው ወደ ስራው እንደሚገባም ታውቋል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂ አስፈረመ

መሳይ አያኖ አዲሱ የኢትዮጵያ ቡና የግብ ዘብ ሆኗል። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሚሳተፈው...

ሲዳማ ቡናዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

የሲዳማ ቡና ቡድን መሪ ታገደ

በዮሴፍ ከፈለኝ የፕሪምየር ሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የቡድን መሪው የቀድሞው ዳኛ ዕግድ...

ዜናዎችየዲሲፕሊን ውሳኔዎች

27ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች አብዱላጢፍ ባምባ (መቐለ 70 እንደርታ) : ክለቡ ከ ወልዋሎ አዲግራት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሲዳማ ቡና የሊጉን መሪነት ሲያጠናክር ኤሌክትሪክ እና አፄዎቹም አሸንፈዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን ጨዋታ ሲዳማ ቡና ፣ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እና ፋሲል...