የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና የግብ ዘብ ከዛሬ ምሽቱ ጨዋታ ውጪ ሆኗል።
በትላንትናው ምሽት ዘገባችን እንደጠቆምነው የዛሬ አመት በሀገሩ ዩጋንዳ ፕሪምየር ሊግ ለኤክስፕረስ ቡድን ሲጫወት ከኪታራ ክለብ ጋር ቡድኑ ባደረገው ጨዋታ ላይ በቋሚ አሰላለፍ ተካቶ የነበረው የአሁኑ የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ ኢማኑኤል ካልም 7ለ0 በሆነ ውጤት ክለቡ በወቅቱ ሺሸነፍ ከአወራራጅ የቤቲንግ ድርጅቶች ጋር በፈጠረው ግንኙነት ውጤቱ በዚህም መልክ እንዲሰፋ ጨዋታውን በማጭበርበር ገንዘብ ተቀብሏል በሚል የዩጋንዳ እግር ኳስ ፌድሬሽን ለአስራ አንድ ወራት ምርመራን ካደረገ በኋላ በያዝነው አመት ሲዳማ ቡናን ከኤክስፕረስ ክለብ መቀላቀል የቻለው ይህ ዩጋንዳዊው የሰራው ጥፋት በማስረጃ በመረጋገጡ የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌድሬሽን ከማንኛውም እግር ኳስ ለማገድ ተገዷል።
ይህንንም ተከትሎ በዛሬው ዕለት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ስታዲየም ላይ የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ከስሑል ሽረ ጋር ጨዋታውን ሲያደርግ ይህ ግብ ጠባቂ ከአሰላለፍ ውጪ ሆኖ በምትኩ መስፍን ሙዜ ወደ ቋሚ አሰላለፍ ተካቷል።
ክለቡ ሲዳማ ቡና በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን በኩል የዕግዱ ውሳኔው በደብዳቤ ባይደርሰውም ባለበት ፍራቻ ተጫዋቹም ላለመጠቀም መወሰኑን አረጋግጫለሁ።
አስተያየት ይስጡ