By using this site, you agree to the Privacy Policy and Terms of Use.
Accept
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Reading: ታሪካዊው ክለብ በውስብስብ ፈተናዎች ውስጥ እስከ መቼ ?
Share
Notification Show More
Latest News
ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ
ዜናዎች የኢትዮጵያ እግርኳስ ዳኞች ማህበር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን
በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ኢትዮጵያ ቡና ዜናዎች
አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዝውውር ዜናዎች ዜናዎች አርባምንጭ ከተማ
የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዜናዎች የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Aa
ሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያሀትሪክ ስፖርት ኢትዮጵያ
Aa
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
  • መነሻ ገፅ
  • ዜናዎች
  • ፕሪሚየር ሊግ
    • ባህርዳር ከተማ
    • ወላይታ ዲቻ
    • ድሬዳዋ ከተማ
    • ፋሲል ከነማ
    • ሲዳማ ቡና
    • አዳማ ከተማ
    • ሀዋሳ ከተማ
    • ቅዱስ ጊዮርጊስ
    • ኢትዮጵያ ቡና
    • ጅማ አባጅፋር
    • ወልቂጤ ከተማ
    • ሰበታ ከተማ
    • ሀዲያ ሆሳዕና
  • ዋልያዎቹ
  • ውድድሮች
  • English Article
  • French Articles
  • ስለ እኛ
Have an existing account? Sign In
Follow US
  • Advertise
© 2023 Hatrick Spoert. Design by Tech-ethiopia.com All Rights Reserved.
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግዜናዎችቅዱስ ጊዮርጊስ

ታሪካዊው ክለብ በውስብስብ ፈተናዎች ውስጥ እስከ መቼ ?

ቴዎድሮስ ታከለ
ቴዎድሮስ ታከለ 2 months ago
Share
SHARE

ታሪክን ሰንዶ ገደል አፋፍ ለቆመው ቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ክለብ ለበሽታው መድሀኒትን ወይስ የከፋ በሽታ …? በሚል ዘርዘር ባለ መልኩ ይህንን ሀሳብ እንካቹ ብለናል !

በኢትዮጵያ ውስጥ እግር ኳስን በብዙሀኑ ልብ ውስጥ ታትሞ እንዲቀር ከነጮች ጋር ትግል ውስጥ በመግባት ሀገሪቷ ላይ ተወዳጅ ስፖርት ሆኖ ዛሬም ድረስ እንዲቀር የቅዱስ ጊዮርጊስን ያክል ሚና ያለው ክለብም ሆነ የሚስተካከለው የለም ፣ የኢትዮጵያን የእግር ኳስ ታሪኮቿን ላገላበጠ ከፊት ራሱን ያሰፈረው ይህ ዘመን ተሻጋሪው ክለብ እንደሆነ ማንም የማንንም ምስክር ሳያሻ ታሪኩን እና ስኬቱን የተመለከተ ሁሉ በቀላሉ መረዳት ይችላል።

የቅዱስ ጊዮርጊስን መለያ ላለፉት እልፍ አመታት የለበሱ አስልጣኞች እና ተጫዋቾች በተለያዩ አጋጣሚዎች ክለቡ የአሸናፊነት ምልክት እና የድል መሠረት እንደሆነ ደጋግመው ሲናገሩ የሚደመጥ ሲሆን ይህንንም ንግግር ለማረጋገጥ ቡድኑ ያገኛቸውን ለቁጥር የሚያዳግቱ ዋንጫዎችን አስተውሎ ምን ያህል እልፍ የድል ጥጋቦችን እንደሸመተ በክለቡ ውስጥ ላሉም ሆነ ለነበሩትም ብቻ ሳይሆን እንዲሁ ለተመለከቱ እና ታሪኩንም ለሰሙ በሙሉ ልብን የሚያሞቅ የደስታ ሲቃ ብቻ ባለቤት መሆን እንደቻለ ማረጋገጥ ይቻላል። ቅዱስ ጊዮርጊስ በርካታ ተጫዋቾችን አፍርቷል ለራሱ ብቻም ሳይሆን ለሀገርም ጭምር እንካቹ ብሎ ለግሷል ፣ በተለያዩ ክለቦች የሚጫወቱ ተጫዋቾችም የክለቡን መለያ ለመልበስ ትልቁ ህልማቸው እንደሆነ በተደጋጋሚ ሲያነሩ የሚሰማ ሲሆን በለስ ቀንቷቸው ቡድኑን የሚቀላቀሉትም በገንዘብ ሆነ በስም ከፍ ያለውን ቦታ ሲያገኙ ህይወታቸውም የተቃና መንገድን ሲሻ ይስተዋልም ጭምር ነበር።

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከአመታት በፊት በገንዘብም ይሁን በትልልቅ ስፖንሰሮች በመደገፍ ከሀገራችን እግር ኳስ ክለቦች የገዘፈ ስም የነበረው ሲሆን ክለቡ በሀብት በተንበሸበሸበት በእነዛ አመታት እንደ ክለብ ቡድኑ ራሱን እንዲችል ክለቡን ይመሩ የነበሩ አመራሮችም ይሁኑ ግለሰቦች እንዳላቸው ሀብት መዋለ ንዋይ መሠረተ ልማት ፣ የገበያ አዳራሾች ፣ ህንፃዎች ፣ ሆቴሎች እና መጠነኛ ሜዳዎች እና ዘመናዊ ስታዲየሞችን ገንብተው ክለብ እፎይ እንዲል ማድረግ ሲጠበቅባቸው ገንዘብ አለ ሌላ ወጪን እንቢ በሚል አጉል ብሂል ከኪስ ማውጣትን እንጂ ክለቡ ነገ ምን ያስፈልገዋል ? እንዳይቸገርስ የራሴ የሚለውስ ምን ሊኖረው ይገባል ? የሚል አስተሳሰብን በዕቅዳቸው ማካተት ሳይችሉ በመቅረታቸው ክለቡ አሁን ላይ ላለበት ፈታኝ ቁመና ላይ እንዲገኝ ዳርጎታል።

- ማሰታውቂያ -

እንደ ሀገር ስሙ በማይፋቅ መዝገብ ላይ ተፅፎ ለዘመናት ተጫዋቾች የቅዱስ ጊዮርጊስን መለያ ለመልበስ የሚናፍቁለት ያ ስመ ገናናው ክለብ በግለሰቦች የግል ንትርክ እና ራስ ወዳድነት ብዙሀኑ የእኔ የሚለው የህፃኑም ፣ የወጣቱም ፣ የአዛውንቱም የሆነው ክለብ ዛሬ ግን ስሙን ብቻ ይዞ በብዙ ፈተናዎች ውስጥ መጓዙን ቀጥሏል። ያ ከፍ ባለ ገንዘብ ብቻ ስፖንሰር ፈላጊ የነበረው ግለሰቦችም ባላቸው ጊዜ ለክለቡ የሀብት ምንጭ መፍጠር ያልቻሉለት በአንድ ወቅትም ከኢትዮጵያም አልፎ በአፍሪካ አህጉር ከሚጠሩ ትልልቅ ክለቦች መካከል ስሙ በጉልህ የሰፈረው ፈረሰኛ አሁን ደመወዝ መክፈል አቅቶት ፣ ክለቡን ከፍ በማያደርግ ትንንሽ ስፖንሰሮች መዳፍ ስር ለመውደቅ ተገዷል።

ብዙሀኑ የቆሰሉለት አለፍ ሲልም የሞቱለትን ክለብ ለማዳን ከግለሰቦች አስተሳሰብ በመውጣት ሁሉም የክለቡ ወዳጅ በሚጠቅመው ፣ ክለቡም በገንዘብ ራሱን ቀና ወደሚያደርግበት መንገድ እንዲመጣ እሹሩሩ ሳይሆን ተግባር ላይ ብቻ ሊያተኩር ብቻ እና ብቻ ያስፈልጋል እና ታሪክን ሰንዶ ገደል አፋፍ ለቆመው ክለብ ለበሽታው መድሀኒትን እንጂ የከፋ በሽታ አያስፈልገውም እና ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ግድ ይላል።

You Might Also Like

ኢንተርናሽናል አርቢትር ማኑኤ ወ/ጻዲቅ ከአዳማ ተሰናበተ

በረከት አማረ ወደ ቀደመ ክለቡ ሊመለስ ይችላል ?

አርባምንጭ ከተማ ሴኔጋላዊ አማካይ አስፈረመ

አርባምንጭ ከተማ ጋናዊ አጥቂ አስፈረመ

የ22ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

Share this Article
Facebook Twitter Email Print
Previous Article የ13ኛ ሳምንት የዲሲፕሊን ውሳኔዎች
Next Article ነገሌ አርሲ ማስገረሙን ሲቀጥል ቀሪ ሁለት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል

Follow US

Find US on Social Medias
127k Like
2.9k Follow
1.6k Follow
19.7k Follow

Weekly Newsletter

Subscribe to our newsletter to get our newest articles instantly!

ተነባቢ ዜናዎች
Uncategorized

​የወልዲያ ስታዲየም የመግቢያ ዋጋ ላይ ማስተካከያ አደረገ 

hatricksport team By hatricksport team 9 years ago
የጨዋታ ዘገባ | አዳማ ከተማ ከአስር ድል አልባ ጨዋታዎች በኋላ አሸንፏል
ፋሲል ከነማ ከ ድሬዳዋ ከተማ | ቀጥታ የውጤት መግለጫ
የጨዋታ ዘገባ | መከላከያ በድጋሚ ቅዱስ ጊዮርጊስን ነጥብ አስጥሏል
Central Paris Rents Fall 15% While Rural Areas Rise
- Advertisement -
Ad imageAd image
Global Coronavirus Cases

Confirmed

0

Death

0

More Information:Covid-19 Statistics
about us

Phone: 0993808668 Email: [email protected] .

Find Us on Socials

© Hatrick Sport 2023 All Rights Reserved.

Removed from reading list

Undo
 

Loading Comments...
 

    Welcome Back!

    Sign in to your account

    Lost your password?