ለቀጣዮቹ አምስት አመታት ቅዱስ ጊዮርጊስን በቦርድ አመራርነት እንዲመሩ በቅርቡ የተመረጡ ግለሰቦች ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት አሞርቷል።
በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ከፊት ስሙ የሚጠራው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከቅርብ አመታት ወዲህ በክለቡ ውስጥ የተለያዩ ችግሮች እየተስተዋሉ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን ከእነኚህም ዋነኛው በየአምስት አመቱ ምርጫ የሚደረግበት የቦርድ አመራሮች ምርጫ ይጠቀሳለ። በአቶ አብነት ገብረመስቀል የሚመራው የክለቡ ቦርድ ምርጫ ማድረግ ከነበረበት ወቅት ከሰባት አመታቶች በላይ ጊዜውን ቢጨርስም እየመራ ቆይቶ ከሳምንታት በፊት ጥቅምት 16 በቀድሞው ግሎባል በአሁኑ ኢትዮጵያ ሆቴል ላይ ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ ሁለት መልኮች በነበሩት እና አጨቃጫቂ ጉዳዮች በዕለቱ ቢነሳም በክለቡ ደንብ መሠረት ምርጫ መደረግ አለበት በሚል አቶ አብነት ገብረመስቀል በቦታው በድጋሚ የቦርድ ሰብሳቢ በማድረግ አቶ ንዋይ በየነ እና ሚሊዮን በየነን ከነበራቹ ቀሪዎቹ አምስት አዲስ አመራሮችን በመምረጥ መቋጨቱ ይታወሳል።
ይሁን እንጂ የክለቡ አንዳንድ ደጋፊዎች ምርጫው አግባብነት የለውም በሚል ጉዳዩን ወደ ፌድራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመውሰድ አዲስ የተመረጠው የስራ አመራር ቦርድ እንዲታገድ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን ይህንን የዕግድ ጉዳይም የአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ፣ የኢፌድሪ የባህል እና ስፖርት ሚኒስትር እንዲሁም የአዲስ አበባ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽኖች የማስፈፀም ሀላፊነት እንዲወስዱም ታዟል።



