ሲዳማ ቡና በሁለት አመት ውል ከድቻ ጋር ለመቀጠል የተስማማውን ተከላካይ በእጁ አስገብቷል።
በአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ አማካኝነት ወዳሳደገው ክለብ ወላይታ ድቻ ተመልሶ የመጫወት ዕድልን ያገኘው ወጣቱ የመሐል ተከላካይ ውብሸት ክፍሌ ሲዳማ ቡናን በሁለት አመት ኮንትራት በይፋ ተቀላቅሏል።

ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት በልጅነት ክለቡ ወላይታ ድቻ ቆይታን ያደረገው የቀድሞው የቦዲቲ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ተጫዋች ባለፈው ሐሙስ አመሻሽ በወላይታ ድቻ ኮንትራቱን ያራዘመ ቢሆንም ወዳሳደገው ክለብ ወላይታ ድቻ ተመልሶ እንዲጫወት የረዳውን የአሰልጣኝ ያሬድ ገመቹን ጥሪ ተቀብሎ ከኤፍሬም ታምራት በመቀጠል የሊጉን ሻምፒዮን ሲዳማ ቡናን በሁለት አመት ውል ተቀላቅሏል።
አስተያየት ይስጡ