አሰልጣኝ ገብረመድህን ሐይሌ ሁለተኛውን አዲስ ፈራሚ ወደ ክለባቸው አካተዋል።
ትላንት አመሻሹን ግብ ጠባቂው አቡበከር ኑራን ወደ ስብስባቸው ያካተቱት ቡናማዎቹ በዛሬው ዕለት ሁለተኛ ፈራሚያቸውን አግኝተዋል።

ለትውልድ ሀገሩ ክለብ ሀድያ ሆሳዕና በሁለት አጋጣሚዎች የተጫወተው የቀድሞው የአርባምንጭ ከተማ ፣ ወላይታ ድቻ እና የተጠናቀቀውን የውድድር ዘመን ደግሞ በኢትዮ ኤሌክትሪክ ያሳለፈው የመሐል ተከላካዩ በረከት ወልደዮሐንስ ኢትዮጵያ ቡናን በሁለት አመት ዛሬ ካደረገው የህክምና ምርመራ በኋላ መቀላቀሉ ተረጋግጧል።
አስተያየት ይስጡ