ወደ ቀደመ ክለቡ ሊያመራ ከጫፍ ደርሶ የነበረው አማካይ በመጨረሻም የሊጉን መሪ ምርጫው አድርጓል።
ከአሜሪካው ሎዶን ዩናይትድ መልስ የቀድሞው ክለቡን ፋሲል ከነማን ለመቀላቀል ከክለቡ አመራሮች ጋር ንግግር ማድረግ ጀምሮ የነበረው አማካዩ ሱራፌል ዳኛቸው የክለቡ የበላይ አካላት ከክፍያ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ባነሱት ጉዳይ ተጫዋቹ ወደ ክለቡ ማምራት ሳይችል ቀርቷል።
በመሐል የአማካዩ ፈላጊ ሆኖ ብቅ ያለው ተጫዋቹ በመጨረሻም ለሲዳማ ቡና ፈርሟል። ተጫዋቹ ተጥሎበት የነበረውን ዕግድም ተግባራዊ አድርጓል።
አስተያየት ይስጡ