ሀትሪክ ስፖርት ከቀናቶች በፊት ፈጣኑ አጥቂ ሲዳማ ቡናን እንደሚቀላቀል ነግራችሁ የነበረችው መረጃ ዛሬ በይፋ ተረጋግጧል።
ከአቃቂ ቃሊቲ እግርኳስን ጀምሮ በሐረር ሲቲ ፣ ደደቢት ፣ ፋሲል ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተጫወተ በኋላ ወደ ግብፅ በማምራት ዜድ በተባለ ክለብ አንድ አመት ከስድስት ወራት ቆይታን አድርጎ በድጋሚ ወደ ሀገር በመምጣት ለመቻል ከፈረመ በኋላ በመጨረሻም ግን ወደ ግብፅ ከማምራቱ በፊት የሊጉን ዋንጫ ወዳነሳበት ቅዱስ ጊዮርጊስ በቅፅበት በመመለስ ያለፉትን ወራት በክለቡ እየተጫወተ የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ዝርዝር ውስጥ በ8 ጎሎች መቀመጥም ችሏል።
በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ውል ቢኖረውም ከቀናት በፊት ይፋ እንዳደረኩላችሁ አጥቂው ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር በመለያየት ወደ ሲዳማ ያመራል ብለናችሁ የነበረ ሲሆን በከፍተኛ የገንዘብ ክፍያም በይፋ የሊጉን መሪ ተቀላቅል።
አስተያየት ይስጡ