ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የተለያየው አጥቂ የሊጉን መሪ ሊቀላቀል ነው።
ከአቃቂ ቃሊቲ እግርኳስን ጀምሮ በሐረር ሲቲ ፣ ደደቢት ፣ ፋሲል ከነማ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተጫወተ በኋላ ወደ ግብፅ በማምራት ዜድ በተባለ ክለብ አንድ አመት ከስድስት ወራት ቆይታን አድርጎ በድጋሚ ወደ ሀገር በመምጣት ለመቻል ከፈረመ በኋላ በመጨረሻም ግን ወደ ግብፅ ከማምራቱ በፊት የሊጉን ዋንጫ ወዳነሳበት ቅዱስ ጊዮርጊስ በቅፅበት በመመለስ ያለፉትን ወራት በክለቡ እየተጫወተ የሊጉ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ዝርዝር ውስጥ በ8 ጎሎች መቀመጥም ችሏል።
በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ውል ቢኖረውም “ክለቡ የገባልኝን ቃል መፈፀም አልቻለም ታገስኩኝ ምንም ደመወዝ በሌለበት ቤተሰቤ መቸገር የለበትም አሁን ይበቃኛል ብዙ ነገር ጥዬ ብመጣም የሚሰማኝ የለም እንዲያስተካክሉም ስድስት ወር ጠበኩኝ አሁን ግን ይበቃኛል ከራሴ እያወጣው መጓዝ የለብኝም” ሲል ከቀናት በፊት በስልክ የነገረን አጥቂው በወኪሉ አማካኝነት ለፈረሰኞቹ ያስገባው የመልቀቂያ ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ ፈጣኑ አጥቂ የሊጉን መሪ ሲዳማ ቡናን ሊቀላቀል ከጫፍ መድረሱን ያገኘነው መረጃ ጠቁሟል።


