ከትላንት በስቲያ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በወሰነው ውሳኔ ላይ ቡድኑ ውሳኔውን እንዲያጤን አሳስቧል ።
ሰኔ 1 በኢትዮጵያ ዋንጫ ሲዳማ ቡና ከ ወላይታ ድቻ ያደረጉት ጨዋታ ጨዋታውን በእኛ አሸናፊነት ማለትም (በሲዳማ ቡና ) አሸናፊነት ያጠናቀቅን ሲሆን የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ያለ አግባብ ለወላይታ ድቻ ይሰጥ በማለት የወሰኑት ውሳኔ እንደሚቃወሙ በደብዳቤ ገልፀዋል ።
ቡድኑ ቅሬታ ወይም ይግባኝ ለማስገባት በተቀመጠው የቀን ገደብ መሰረት በዛሬው እለት የቅሬታ ደብዳቤውን ማስገባቱን የገለፀ ሲሆን ሀገራችን የ FIFA የእግር ኳስ መተዳደሪያ ደንቦች በመጥቀስ በውሳኔው ላይ ቅሬታቸውን የገለፁ ሲሆን የእርምት እርምጃ እንዲወስድ አሳስበዋል ።
ሲዳማ ቡና የመጀመሪያ ምዕራፍ ህጋዊ ሂደቱን በተከተለ መልኩ ለፌዴሬሽኑ ቅሬታ ደብዳቤ ማስገባቱን የገለፀ ሲሆን በቀጣይ ምላሽ የማያገኝ ከሆነ ህጋዊ ሂደቶችን እየተከተለ ወደ ተለያዮ ምዕራፎች እንደሚያመራ በደብዳቤው ገልፆል ።
- ማሰታውቂያ -



