✅ ከክልል ክለቦች ሻምፒዮና እስከ ኢትዮጵያ ቡና የ አዶላ ወዩ ፈርጥ አንተነ ተስፋዬ የሳምንቱ ተረኛ እንግዳችን ነው !
ሀትሪክ : በቅድሚያ ቃለመጠይቅ ለማድረግ ፍቃደኛ ስለሆንክ እናመሰግናለን !
አንተነህ : እኔም አመሰግናለሁ !!
ሀትሪክ: ኢትዮጵያ ቡናን እንዴት ልትቀላቀል ቻልክ ?
- ማሰታውቂያ -

አንተነህ :ኢትዮጵያ ቡናን የተቀላቀልኩት መንገድ 2014 ክርምት ላይ ክልል ክለቦች ውድድር ላይ ሀዋሳ እየተወዳደርን እያለ በዛን ሰአት አሰልጣኝ ተመስገን ዳና የሙከራ ግዜ ሰቶኝ በዛ መንገድ ልፈርም ችያለሁ
ሀትሪክ :ለኢትዮጵያ ቡና ስትፈርም ምን ተሰማህ ?
አንተነህ :እኔጃ በሰአቱ የተሰማኝን ስሜት እንደዚህ ነው ብሎ ማውራት በጣም ከባድ ነው ከእኔ አልፎ የሀገሬ ልጆች አዶላ እና ሻኪሶ የለውን ህዝብ ደስታ ሳይ በጣም እድለኛ እንደሆንኩኝ ነው የተሰማኝ
ሀትሪክ: አንተ በምትጫወትበት አጥቂ ቦታ ለአንተ ምርጡ ማነው ??..
አንተነህ : አቡበከር ናስር
ሀትሪክ : በሀገራችን ትልቁ ጨዋታ ላንተ ማን ከማን ጋር ሲጫወቱ ነው ??
አንተነህ : ምን ጥያቄ አለው ኢትዮጵያ ቡና ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ

ሀትሪክ : በብዛት የሀገራችን እግር ኳስ ተጨዋቾች በተለምዶ ከባድ ትሬሊግ አይወዱም ይባላል አንተ ከየትኛው ነህ ?
አንተነህ : እንዳዛ እንኴን ልክ አይመስለኝም እኔ አሰልጣኜ የሰጠኝን ማንኛውንም ስራ ሰራለው አስፈላጊ በሆነበት ሰአት ደሞ በግሌ ሰራለው !
ሀትሪክ: ከልምምድ በሃላ በምን አይነት መልኩ እረፍት ታደርጋለህ
አንተነህ : ተኛለው ከዛ ፕላይስቴሽን እጫወታለሁ ወይም ሶሻል ሚዲያ እጠቀማለሁ !
ሀትሪክ : ፎደን ብለን ጋርዲዮላ ካልን አንተነህ ብለን ማን እንላለን ?
አንተነህ : ምንም ጥርጥር የሌለው አሰልጣኝ ተመስገን ዳና !
ሀትሪክ : የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ እንዴት ትገልፃቸዋለህ
አንተነህ : እውነት ለመናገር ቃላት ያንሰኛል የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ለሊጋችን ድምቀት እና ውበት ነው በጣም ብዙ ሰውነትን ሚነዝሩ መዝሙሮች ደሞ ሌላ አለም ውስጥ እንድትገባ ነው ሚያረገው በጣም ልዩ ናቸው !!
ሀትሪክ : በሊጉ ካለፉት ዓመታት ምን ተማርክ ??
አንተነህ : ብዙ ነገሮችን ተምርያለሁ እሰካሁን አብረውኝ ከተጫወቱትም ከተቃራኒ ቡድንም !
ሀትሪክ : ኮንተራትክ ተጠናቋል በቀጣይ ምን እንጠብቅ ?
አንተነህ : እኔጃ እስካሁን በእሱ ጉዳይ የወራነው ነገር የለም ግዜው ገና ነው ወደፊት ሚሆነውን እናያለን !
ሀትሪክ : በኢትዮጵያ ቡና ማለያ ከገጠምካቸው በጣም ከባዱ ተከላካይ ላንተ ማነው ??
አንተነህ : አንድ ተጫዋች ብቻ አደለም አሉ ብዙ ናቸው
ሀትሪክ : ካስቆጠርካቸው ጎሎች ላንተ ማን ላይ ያስቆጠርከው ጎል ምርጡ ነው ??
አንተነህ : አርባምንጭ ላይ በህርዳር ስታዲየም ከሊጉ ጋር የአሰተዋወቀኝን ጎል መርጣለው።
ሀትሪክ : ከኢትዮጵያ ቡና ሙዝሙሮች የትኛውን ትወዳለህ ??
አንተነህ : ሁሌ ወደ ጫወታ ስንገባ ምንዘምረው መዝሙር (ተወዳጅ ዝነኛው ክለባችን)ሚለውን

ሀትሪክ : የማን ደጋፊ ነህ ከተጫዋቾች ማንን ታደንቃለህ ?
አንተነህ : ማንችስተር ዩናይትድ ከተጨዋች ደግሞ ሮናልዶ አድናቂ ነኝ ።
ሀትሪክ : ክረምቱን እንዴት ልታሳልፍ አስበሀል ??
አንተነህ : አሁን በትሬኒንግ እያሳለፍኩኝ ነወ ከጉዳት ተመልሼ ሙሉ ለሙሉ በቀን 2ጊዜ ጂም እና ሜዳ ላይ እየሰራው ነው ።
ሀትሪክ : የአንተነህ ተፈራ ምንግዜም ምርጥ 11 እነማን ናቸው ???
አንተነህ :- በረኛ ዳንኤል ዳንግል
ተከላካይ : ሄኖክ አዱኛ፣ረመዳን የሱፍ ፣ፈቱዲን ጀማል ፣ ያሬድ ባዬ
አማካይ : ሀይደር ሸረፋ፣ ሽመልስ በቀለ፣ አቡዱልከሪም ወርቁ ፣
አጥቂ : ጌታነህ ከበደ ፣ ቸርነት ጉግሳ እና ዳዋ ሆጤሳ !!
ሀትሪክ : በመጨረሻ ቀረ ምትለው ካለ ወይም ማመስገን ምትፈለገው ካለ ??
አንተነህ : በመጀመሪያ እስከዚች ሰአት በሰላም ላደረሰን ለድንግል ማርያም ልጅ ምስጋና አቀርባለው በመቀጠል ከኔ በላይ ለኔ ጥሩ ደረጃ ለመድረስ ትልቅ ዋጋ ለከፈሉት ቤተሰቦቼ እንዲሁም ከታች ጀምሮ እስካሁን ላለሁበት ቦታ እውቀታቸውን ሳይሰስቱ ለለገሱኝ አሰልጣኞቼ በመጨረሻም በየትኛውም ሁኔታ ላይ ሆነን እንኳን ያላቸው ሳይሰስቱ ከክልል ክልል ብዙ ነገራቸውን ሰውተው ለሚከተሉን የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ትልቅ ክብር እንዳለኝ መናገር እፈልጋለው ።
ሀትሪክ : ጊዜህን ሰተህን ፍቃደኛ ስለሆንክ በድጋሚ እናመሰግናለን ።
አንተነህ : እኔም ከልብ አመሰግናለሁ ።


