ባሳለፍነው የውድድር ዓመት በ ልደታ ክ/ከተማ ማራኪ እግር ኳስን ሲያስመለክተን የነበረው አሰልጣኝ ኤርሚያስ ዱባለ የኢትዮ ኤሌክትሪክ ሴቶች ቡድን ዋና አሰልጣኝ ለመሆን ተስማማ ። አሰልጣኙ የወረቀት ስራዎችን በመጨረስ ለቡድኑ ፍርማውን እንደሚያኖር ይጠበቃል።
▻ አሰልጣኝ ኤርሚያስ ከዚህ በፊት በኢትዮ ኤሌክትሪክ የመሰረት ማኔ ምክትል በመሆን መስራት የቻለ ሲሆን በሴቶች ኢትዮጵያ ቤሄራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ እንዲሁም በንግድ ባንክ ለረዥም ግዜ በምክትል አሰልጣኝነት አገልግሏል ። አሰልጣኙ በቀጣይ ቀናት ፍርማውን በማኖር ወደ ዝውውሩ የሚገባ ይሆናል ።



