ቢያድግልኝ ኤሊያስ ወደ ሰበታ ከተማ ለመግባት ተስማምቷል፡፡

 

አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱን የቀጠረው ሰበታ ከተማ ቢያድግልኝ ኤሊያስን ለማስፈረም መስማማቱ ታውቋል፡፡

ለ2013 ትላንት ልምምዱን በይፋ የጀመረው ሰበታ ልምደ ብዙ ተከላካይ ሲያፈላልግ ቆይቶ አይኑን ቢያድግልኝ ኤሊያስ ላይ አሳርፏል፡፡ ተጨዋቹ ነገ የኮቪድ ምርሐራውን ካደረገ በኋላ የሰበታ ቡድንን ይቀላቀላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በ2012 የመቀለ 70 እንደርታ ተሰላፊ የነበረ ሲሆን ጠንካራ ተከላካይ ሆኖ ውሉ ያልታደሰበት ምክንያት አሁን ድረስ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport