የኢትዮጲያ አየር ሃይል ከ10 በላይ የስሁል ሽረ ተጨዋቾቾችን ከሽረ ከተማ አውጥቷል

 

በትግራይ ክልል በተካሄደ ህግ የማስከበር ዘመቻ ሽረ እንደስላሴ ነጻ መሆኗን ተከትሎ ወደ 16 የሚጠጉ የስሁል ሽረ ተጨዋቾች ደብረዘይት መድረሳቸው ታውቋል፡፡

ምሽቱን በተገኘ መረጃ በኢትዮጲያ አየርሃይል ኢሊኮፕተር ከ12 ቀናት ድምጽ ማጥፋትና የቤተሰቦቻቸው ጭንቀት በኋላ ተጨዋቾቹ ደብረዘይት መግባታቸው ታውቋል፡፡

ቀሪ የስሁል ሽረና የወልዋሎ አዲግራት የቡድን አባላት በቀጣዮቹ ቀናት ከትግራይ ክልል ይወጣሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን የኢትዮጲያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመር ተስፋን ያለመለመ ሆኗል፡፡

Editor at Hatricksport

Facebook

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport