ምንተስኖት አሎ ወደ አዲስ ክለብ አምርቷል !

 

በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ላይ ብቃታቸውን ካሳዩ ግብ ጠባቂዎች አንዱ የሆነው ምንተስኖት አሎ ከስሑል ሽሬ ጋር መለያየቱ ታውቋል ፡፡

ምንተስኖት አሎ በተቋረጠው የውድድር አመት ወደ ሊጉ ማደግ የቻሉትን ሰበታ ከተማዎች ለመቀላቀል መስማማቱ ይፋ ሆኗል ፡፡

ተስፈኛው ግብ ጠባቂ ምንተስኖት አሎ በተለይም የጣና ሞገዶቹ ወደ ሊጉ ባደጉበት ዓመት ጉልህ ሚናን ሲጫወት በተቋረጠው የውድድር ዓመት ላይም በተከታታይ አራት ጨዋታዎቸ ላይ መረቡን ሳያስደፍር በመውጣት አመርቂ ብቃቱን ዳግም አሳይቷል ፡፡

ምንተስኖት አሎ በውድድር ዓመቱ አጋማሽ ወደ ቱርኩ አንታላያስፖር በማቅናት የሙከራ ጊዜን አሳልፎ መምጣቱ ሲታወስ በብሔራዊ ቡድን ደረጃም ብቃቱን ካሳዪ ግብ ጠባቂዎች አንዱ ነው ፡፡

ምንተስኖት አሎ ዳግም ሰበታ ከተማዎችን ሲቀላቀል ከዚህ ቀደም በፋሲል ከተማ ፤ ባህር ዳር እንዲሁም ስሑል ሽረ በመጫወት ማሳለፉ ይታወቃል ፡፡

ከውበቱ አባተ ጋር መለያየታቸው የሚታወቀው ሰበታ ከተማዎች ክፍሌ ቦልተናን ዳግም ለመቅጠር እያጤኑ መሆኑ ይታወቃል ፡፡

Hatricksport website Editor

Twitter

kidus Yoftahe

Hatricksport website Editor