አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራዉን በዋና አሰልጣኝነት ከቀጠሩ በኋላ ወደ ዝዉዉር ገበያዉ በመግባት የተለያዩ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ላይ የሚገኙት ሰበታዎች አሁን ደግሞ የፊት አጥቂዉን ባየ ገዛኸኝን ማስፈረማቸዉ ተረጋግጧል።
የዉድድር አመቱን ከባህርዳር ከተማ ጋር በጥሩ አቋም ማጠናቀቅ የቻለዉ አጥቂዉ ባየ ገዛኸኝ በሁለት አመት የስምምነት ዉል ሰበታ ከተማን መቀላቀሉ እርግጥ ሆኖአል።
የቀድሞው የሲዳማ ቡና ፤ ወላይታ ዲቻ እና እንዲሁም ያለፈወን አንድ የዉድድር አመታት በባህርዳር ከተማ ተጫዉቶ ያሳለፈዉ አጥቂዉ አሁን ደግሞ የቀድሞ አሰልጣኙ ዘላለም ሽፈራዉ ጋር በሰበታ ከተማ የሚገናኝ ይሆናል።


