በትላንትናው ዕለት በአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ እየተመሩ በርካታ ተጫዋቾችን ወደ ስብስባቸዉ የቀላቀሉት ጅማ አባጅፋሮች በዛሬዉ ዕለት ደግሞ አጥቂዉን የኋላሸት ፍቃዱ ሲያስፈርሙ በተጨማሪም የአራት ነባር ተጫዋቾቻቸውን ዉል አድሰዋል።
የዉድድር አመቱን በአዳማ ቤት ማሳለፍ የቻለዉ አጥቂዉ የኋላሸት በቅርቡ አሰልጣኝ አሰናፊ በቀለን በዋና አሰልጣኝነት የቀጠሩትን ጅማ አባጅፋሮችን በሁለት አመት የስምምነት ዉል ተቀላቅሏል።
በተጨማሪም ከክለቡ ጋር ለመቀጠል ዉላቸዉን ያራዘሙት ደግሞ ተከላካዮቹ እንዳላሚን ናስር እና ወንድማገኝ ማርቆስ እንዲሁም የመስመር አጥቂዉ ቤካም አብደላ እና የአማካይ ስፍራ ተጫዋቹ አድናን ረሻድ ለሚቀጥሉት ሁለት አመታት በክለቡ የሚያቆያቸዉን የኮንትራት ዉል መፈረማቸዉ ተረጋግጧል።


