መነሻ ገጽ ሰበታ ከተማ ሙጂብ ቃሲም ወደ ሰበታ ከተማ?
ሰበታ ከተማቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግዜናዎችፋሲል ከነማ

ሙጂብ ቃሲም ወደ ሰበታ ከተማ?

አጋራ
አጋራ

*…ለመጨረሻ ውሳኔ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንትና ዋና ጸሃፊ ከካሜሩን መልስ ይጠበቃሉ....

የአልጄሪያውን ታላቅ ክለብ ጂ ኤስ ካቢሌን ተቀላቅሏል የተባለው የፋሲል ከነማው ሙጂብ ቃሲም ዝውውር የከሸፈ ይመስላል።

ተጨዋቹ ወደ አልጄሪያው ውጤታማ ክለብ ለ3 አመት ፈርሟል ቢባልም ዝውውሩ በፋሲል ይፋዊ ገጽ ላይ አለመነገሩ አነጋጋሪ ሆኖ ሰንብቷል። ከታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ ግን የሚጠበቅበትን 1.5 ሚሊዮን ብር መልሶ መልቀቂያውን የወሰደው ሙጂብ ለሰበታ ከተማ ሊፈርም ከጫፍ መድረሱን ከታማኝ ምንጭ የተገኘ መረጃ ያስረዳል።
የአልጄሪያው ክለብ ለፋሲል ከነማ 30 ሺህ ዶላር በ5 ወር ውስጥ ለመክፈል ጥያቄ አቅርቦ ፋሲል በመስማማቱ የተጨዋቹ ጉዞ በቀናት ውስጥ ሊፈጸም እንደሆነ ወኪሉ ቢናገርም ዝውውሩ የሚሳካ አይመስልም።

ፋሲል ከነማዎች መልቂያውን ለሙጂብ ቢሰጡም የውጪው ዝውውር ካልተሳካ ለሌላ የሀገር ውስጥ ክለብ መጫወት እንደማይችል ቅድመ ፊርማ ከተጨዋቹ ጋር ከተፈራረሙ በኋላ ተጨዋቹና ስራ አስኪያጁ ውሉን ለኢትዮዽያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማስገባታቸው ታውቋል።

የሙጂብ የአልጄሪያ ጉዞ የመሳካቱ ጉዳይ ያጠራጠረውና በአሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው /ሞውሪንሆ/ ስር ራሱን እያጠናከረ ያለው ሰበታ ከተማ ከሌሎቹ ፈላጊ ክለቦች ፈጥኖ ለማስፈረም ከተጨዋቹ ጋር የተስማማ ቢሆንም ፌዴሬሽኑ ግን ተጨዋቹ ከፋሲል ከነማ ጋር ተፈራርሞ ያስገባውን ደብዳቤ ከግምት በማስገባት ዝውውሩን ለማጽደቅ እንደሚቸገር በመግለጽ ስምምነቱን ካሜሩን የነበሩት ፕሬዝዳንቱ አቶ ኢሳያስ ጅራና ዋና ጸሃፊው አቶ ባህሩ ጥላሁን በነገው ዕለት እስኪመለሱና እስኪወስኑ ድረስ እንዲዘገይ መደረጉ ተነግሯል።

የሙጂብ ወደ አልጄሪያ የመጓዝ እድሉን ፋሲል ከነማ እንዳያበላሽ ከፍተኛ የማሳመን ጥረት ያደረጉት ፕሬዝዳንቱ በመሆናቸው በጉዳዩ ላይ የሚሰጡት አስተዳደራዊ ውሳኔ ይጠበቃል።

ተጨዋቹ መልቀቂያውን በእጁ ስለያዘ ዝውውር የማድረግ ሙሉ መብቱ የርሱ ቢሆንም ፕሬዝዳንቱ ጣልቃ ባይገቡ ኖሮ መልቀቂያውን ላያገኝ ስለሚችልና ፌዴሬሽን ሄዶ የውጪ ጉዞው ካልተሳካ ወደ ፋሲል ለመመለስ በመስማማቱ ፕሬዝዳንቱ ለውጪ እድል ሲባል ከፋሲል ከነማ ባሰጡት መልቀቂያ ለሀገር ውስጥ ክለብ ለመጫወት እንዲጠቀምበት ፍቃዱን ይሰጡታል ወይ የሚለው ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል።
በጉዳዩ ዙሪያ ተጨዋቹና ወኪሉ ወደ አልጄሪያው ክለብ የሚደረገው ጉዞ በሂደት ላይ መሆኑን ከመጥቀስ ውጪ ስለ ሀገር ውስጥ ክለቦች ከማመን ተቆጥበዋል። የፋሲል ከነማውና የሰበታ ከተማን ስራ አስኪያጆች አቶ አቢዮት ብርሃኑና አቶ አለማየሁ ምንዳን ለማናገር ወደ ግል ስልካቸው ብንደውልም የአቶ አለማየሁ ስልክ ዝግ ሲሆን አቶ አቢዮት ግን ጥሪውን ሊመልሱ ባለመፍቀዳቸው ምላሻቸውን ማግኘት አልቻልንም።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...