መነሻ ገጽ ቅድመ ውድድር ዝግጅት የክለቦች ዝግጅት | ነገሌ አርሲ
ቅድመ ውድድር ዝግጅትነጌሌ አርሲዜናዎች

የክለቦች ዝግጅት | ነገሌ አርሲ

አጋራ
አጋራ

የ2019 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊው ነገሌ አርሲ የውድድር ዝግጅቱን ምን እንደሚመስል በዚህ መልኩ ዳሰነዋል።

በ2017 በተደለደለበት የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ ለ የበላይ ከመሆን ባለፈ በአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ሸገርን ከተማን 3ለ1 በመርታት በጥምር የዋንጫ ድል ወደ 2018 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ማደግ የቻለው ነገሌ አርሲ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደጉበት የሀገሪቱ ትልቁ የሊግ ዕርከን ላይ ባሳዳጊ አሰልጣኙ ቱሉ ደስታ መሪነት በሚያስገርም አቅም በፕሪምየር ሊጉ ካደረጓቸው 38 ጨዋታዎች 15 አሸንፎ በ15ቱ አቻ በመውጣት 8 ጨዋታዎችን ደግሞ በመሸነፍ 37 ጎሎችን ከመረብ በማሳረፍ በአንፃሩ 30 ጎል አስናግደው በ7 የግብ ክፍያ ከሊጉ ሻምፒዮን ሲዳማ ቡና በስምንት ነጥቦች ዝቅ በማለት 60 ነጥቦችን ይዘው ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ የሊጉ ክስተት መሆናቸው ጭምር በማስመስከር አመቱን በስኬት ማጠናቀቅ ችለዋል።

ለሁለተኛ አመት የሊጉ ተሳትፎአቸው ከአምናው አቋም በይበልጥ ከፍ ለማለት የአሰልጣኝ ቱሉ ደስታን ፊርማ በክረምቱ ካገኘ በኋላ በመቀጠል ለቡድኑ ቁልፍ ሚና የነበራቸውን ተከላካዩ ሮቦት ሰላሎ ፣ አማካዩ ዳዊት ተፈራ ፣ አማካዩ አለኝታ ማርቆስ ፣ አጥቂው ሀቢብ ከማል ፣ ጋናዊው ግብ ጠባቂ እድሪሱ አቦዱላሂ እና ካሜሮናዊው ተከላካይ ዴዜሬ ፓስካልን ኮንትራት በማደስ ወደ ዝውውሩ ገብተው ሰባት አዳዲስ ተጫዋቾችን ወደ ማስፈረም ችለዋል። አማካዩ ብሩክ ያሬድን ከሀዋሳ ከተማ ፣ አጥቂው መሐመድ ኑርናስር እና የመስመር ተከላካዩ ጀሚል ያዕቆብን ከድሬዳዋ ከተማ ፣ አማካዩ በረከት ግዛውን ከፋሲል ከነማ ፣ የመስመር አጥቂው እንዳልካቸው ጥበቡን ከወልዋሎ ፣ ግብ ጠባቂው ሰይድ ሀብታሙ እና የሀገሩን ክለብ ንሶአትረማንን ለቆ በ2017 አጋማሽ ወደ መቻል የመጣውን ጋናዊውን አጥቂ ኮሊንስ ኮፊን በይፋ ማስፈረም ችለዋል።

በ2019 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን በባቱ (ዝዋይ) ከተማ ከነሀሴ 19/2018 ጀምሮ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን በይፋ የጀመሩት ሰጎኖቹ በጂም እና በሜዳ የተለያዩ የልምምድ ምዕራፎችን ካሳለፉ በኋላ አሰልጣኝ ቱሉ ደስታ ቡድናቸው በልምምድ ወቅት የነበረውን ጠንካራ እና ደካማ ጎን ለማወቅ ሦስት የወዳጅነት ጨዋታዎች እስከ አሁን አድርገዋል። ከሀዋሳ ከተማ ጋር 2ለ2 በዝዋይ እና በነገሌ አርሲ የሚገኙ የስብስብ ቡድኖችን በተመሳሳይ 8ለ0 በመርታት በቀሪዎቹ የዝግጅት ቀናቸው አንድ ተጨማሪ የወዳጅነት ጨዋታን በማድረግ በይፋ ወደ ውድድር የሚገቡ ሲሆን የመጀመሪያ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታቸውን ደግሞ መስከረም 30/2018 በአዲስ አበባ ስታዲየም ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ይጫወታሉ።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ሽረ ምድረገነትዜናዎችየኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ

ምድረ ገነት ሽረ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ውድድር ውጭ ሆነ!

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲሳተፍ የነበረው እና በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ...

መቻልኢትዮጵያ ቡናዜናዎችየዝውውር ዜናዎች

ሁለቱን ተጫዋቾች ሁለቱ ክለቦች ተካፈሉ

ለሁለት ክለብ በመፈረማቸው ቅጣት ላይ የነበሩት ተጫዋቾች ለመቻል እና ለኢትዮጲያ ቡና እንዲጫወቱ...

ካፍዜናዎች

የኒጀር እና ሞሮኮ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ሊመራ ነው

ራቫት ላይ የሚደረገው ወሳኙ የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ በኢትዮዽያዊያን ዳኞች ይመራል። ኬኒያ...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በ5 ሳምንታት 39 ጨዋታዎች፣ 72 ጎሎችና ከ22.6 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተመዘገበ!

በአቤኔዘር አበበ በ2019 ዓ.ም የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያዎቹ አምስት የውድድር ሳምንታት...