የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በ11 ፌዴሬሽኖች ተከሰሰ

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አባል የሆኑ 11 ፌዴሬሽኖች የኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶክተር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ ህገወጥ አሰራርና የኦሎምፒክ ቻርተርን የጣሰ የምርጫ ሂደትን በመቃወም ለአለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ክስ አቀረቡ።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ምክትል ዋና ጸሃፊ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ የምርጫ መመዘኛውን የተቃወመው አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ብቻ ነው ቢሉም ለአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ቶማስ ባህ በተጻፈው ደብዳቤ የኦሎምፒክ ኮሚቴውን አምባገነናዊ አሰራርና የህግ ጥሰትን በመቃወም 11 ፌዴሬሽኖች ክሱን ማቅረባቸው ታውቋል።
በቀጣይ የአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የሚሰጠው ውሳኔ ይጠበቃል።

ዮሴፍ ከፈለኝ

Editor at Hatricksport