ኒጀር ለወዳጅነት ጨዋታ የምትጠቀምቻውን የ23 ተጫዋቾች ዝርዝር አሳወቀች

የኢትዮጵያ ተጋጣሚዋ ምዕራብ አፍሪካዊት ሃገር ኒጀር በቅርቡ ለምታደርጋቸው ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች የ23 ተጫዋቾችን ዝርዝር አሳወቀች፡፡ ፈረንሳያዊውን አንጋ አሰልጣኝ ጃንሚሸል ካቫሊን መሾሟን በቅርብ ያሳወቀችው ኒጀር ከኢትዮጵያ ጋር ለምታደርገው የደርሶ መልስ ጨዋታ ይረዳት ዘንድ ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎችን ከቻድ እና ከሴራሌዎን ብሔራዊ ቡድኖች ጋር ቀጠሮ መያዟ ይታወቃል፡፡ ይህን ተከትሎም በነዚህ ሁለት ጨዋታዎች የምትጠቀምባቸውን በአብዛኛው በሃገር ውስጥ የሚጫወቱ የ23 ተጫዋቾችን ዝርዝር አሳውቃለች፡፡ በዚሁ ዝርዝር ውስጥ ብሔራዊ ቡድኑን ለረዥም ዓመታት ያገለገሉ ተጫዋቾች የሚገኙበት ሲሆን ዘጠኙ ተጫዋቾች ባሳለፍነው ዓመት ኮት ዲቯርና ማዳጋስካርን የገጠመው ቡድን አባላት የነበሩ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያን ቡድን የሚገጥመው ብሔራዊ ቡድን ከዚህ ዝርዝር ውስጥ የሚገኙ ተጫዋቾች ላይ እነቪክቶሪያን አደባዮርን እና በፈረንሳይ የሚጫወተውን ሴይቡ ኮይታን ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የኒጀር ብሔራዊ ፌዴሬሽን የጠራቸው 23 ተጫዋቾች ዝርዝር ከዚህ በታች ያለውን ይመስላል፡፡

ግብ ጠባቂዎች፡ አብዱራዛቅ ኡማሩ፣ ሙሳ አልዙማ፣ ዳዉዳ ካሳሊ (ናይጄሪያ)

ተከላካዮች፡ አብዱለካሪም ማማዱ፣ ሄርቬ ልቦሂ (ፈረንሳይ)፣ አብዱልናሲር ጋርባ፣ አብዱለራዛከ ሴይኒ፣ ያኩባ ሃማኒ ዲዮሪ (ስፔን) እና አማዱ ሃሩና

የመሃል ሜዳ ተጫዋቾች፡ ኢሳሃ ሳሉ (ዴንማርክ)፣ ማሃማዱ ሳቦ፣ ቡባካራ ጂቦ ታላቱ (ማሊ)፣ ያኦ ካን ፋብሪስ (ሉግዘምበርግ)፣ ኡማሩ ዩሱፍ (ኮት ዲቯር)፣ ዳኒኤል ሱንጉል (ቼክ)፣ ሙሙኒ ዳረንኩም፣ ኡስማን ዲያባቴ (ሳኡዲ አራቢያ)

አጥቂዎች፡ ሃይኔኮይ ሱማና (አልጄሪያ)፣ ሞሃመድ ዋንኮይ (ጊኒ) ኢሳ ጂበሪላ (ቡርኪናፋሶ)፣ ኣማዱ ሙታሪ (ሃንጋሪ)፣ ሃሊዱ ኢድሪሳ እና አብዱላዚዝ ኢብራሂም

Teshome Fantahun

Editor at Hatricksport