ነገሌ አርሲ የፊታችን ሰኞ ልምምድ ይጀምራሉ።
በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደጉበት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ አስደናቂ የውድድር አመትን ማሳለፍ የቻሉት ነገሌ አርሲዎች በቡድናቸው ውስጥ የሚገኙ ወሳኝ ተጫዋቾችን ውል በማራዘም እና አሰልጣኝ ቱሉ ደስታ የሚፈልጓቸውን አዳዲስ ተጫዋቾች ባለፉት ሳምንታት በማስፈረም ያሳለፉ ሲሆን አሁን ደግሞ ለ2019 የሲቢኢ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን መቼ እና የት እንደሚጀምሩ ሀትሪክ ስፖርት አረጋግጧል።
በዚህ መሠረት የፊታችን ሰኞ ነሐሴ 18/2018 በባቱ (ዝዋይ) ከተማ ላይ ዝግጅታቸውን በይፋ ይጀምራሉ።
አስተያየት ይስጡ