በወላይታ ድቻ ታዳጊ ቡድን ፍሬ የነበረው እና ያለፉትን ዓመታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤት ግልጋሎት መስጠት የቻለው በረከት ወልዴ በ 2017 ዓ.ም የከፍተኛ ሊግ ሻምፒዮናዎቹን ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ ደርሷል ።
በረከት ከ ሳምንታት በፊት በ ሸገር ከተማ ለመጫወት መስማማቱን የዘገብን ሲሆን አሁን ወደ ሌላኛው የፕሪሚየር ቡድን ኔጌሌ ለመሄድ በመስማማት ፣ ወደ ባቱ ከተማ የሚገኘው ካምፕ ተቀላቅሏል ።



