ከኢትዮጵያዊ አባት የተገኘውን አማካይ ይዘንላችሁ ቀርበናል።

አባቱ ኢትዮጵያዊ ሲሆን እርሱ የተወለደው ግን በጀርመን ነው። ሞግል ዶርፍ ከተባለ የእግር ኳስ ማሰልጠኛ የተገኘው በአሁኑ ሰዓት ዕድሜው 18 የደረሰው የአጥቂ አማካዩ ኪሩቤል ታዬ። እግር ኳስን አቅልለው ከሚጫወቱ ተጫዋቾች መካከል አንዱ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ተጫዋች በጀርመን ቡንደስሊጋ ተሳታፊ በነበረው እና በአሁኑ ሰዓት በጀርመን ሁለተኛ ሊግ ላይ በሚገኘው ኑረን በርግ ወጣት ቡድን ከ2016 ጀምሮ በመጫወት ላይ የሚገኝ ሲሆን በቡድኑ ከ17 አመት በታች ቡድን ውስጥ ከተጫወተ በኋላ በመቀጠልም ከሁለት አመት በፊት ጀምሮ ደግሞ በዛው በኑረን በርግ ከ19 አመት በታች ቡድን ይገኛል።
በጀርመን ከ19 አመት በታች ፕሪምየር ሊግ እንዲሁም በሌሎች መድረኮች ለኑረን በርግ በሀያ ጨዋታዎች ተሰልፎ ለአንድ ሺህ አምስት መቶ ስልሳ አራት ደቂቃዎች ክለቡን በማገልገል በድምሩ 2 ጎሎችን ያስቆጠረው ተጫዋቹ በቀጣይ ክረምት የኑረን በርግን ዋናውን ቡድን እንደሚቀላቀል የሚጠበቅ ሲሆን የአባቱን ሀገር ኢትዮጵያን ደግሞ በብሔራዊ ቡድን መወከል እንደሚፈለግ ይናገራል።
አስተያየት ይስጡ