የታላቁን ሊቨርፑል መለያን ጨምሮ በጀርመኑ ሆፈንየም እና ሀኖቨር 96 መጫወት የቻለው እና ኢትዮጵያ ውስጥ የተወለደው አማካይ።

ታናሽ ወንድሙ መለሠ ፍራዎንዶርፍ በአሁኑ ሰዓት በጀርመን ቱስ መቸስተር እየተባለ በሚጠራው የእግር ኳስ አካዳሚ ውስጥ እየተጫወተ ይገኛል። እርሱ ግን ለታናሽ ወንድሙ መሠረት መሆን የቻለ ተጫዋች ነው ኢትዮጵያ ውስጥ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከንባታ ጠንባሮ ዞን የተወለደው የ22 አመቱ የመስመር አጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ በሙሉ ስሙ መልካሙ ቤንጃሚን ዳንኤል ፍራዎንዶርፍ በአጭሩ ሲጠራ (መልካሙ ፍራዎንዶርፍ) ይባላል።

አንድ ሜትር ከሰማንያ ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ከተፈጥሮአዊ ቦታው በተጨማሪ በአማካይ እና በአማካይ ተከላካይነት መጫወት የሚችለው ተጫዋቹ የእግር ኳስ ህይወቱን በጀርመኑ ሼፍ ሌንዝ ወጣት ቡድን ውስጥ የጀመረ ሲሆን በመቀጠልም በይበልጥ ወደሚታወቅበት የቡንደስሊጋው ክለብ ሆፈንየም አምርቶም ከክለቡ ወጣት ቡድን ከተጫወተ በኋላ በመቀጠልም በአሰልጣኝ የርገን ክሎፕ የሊቨርፑል የአሰልጣኝነት ቆይታ በተለይ ከጀርመን ወደ እንግሊዝ ካመራ በኋላ በሊቨርፑል ከ18 እና ከ21 አመት በታች ቡድን ውስጥ የነበረውን ጥሩ ተከትሎ በመጨረሻም በገጠመው መጠነኛ ጉዳት ወደ ዋናው ቡድን ሊያሳድጉት ከጫፍ ቢደርሱም በድንገት ወደ ጀርመን ተመልሶ ለሀኖቨር 96 መፈረም የቻለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም በውሰት ውል በጀርመን የታችኛው ክለብ ስቱግ ኪከር እየተጫወተ ይገኛል።

ለጀርመን ከ15 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጀምሮ እስከ ቅርብ ጊዜው የጀመርን ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን ድረስ በተከታታይ ማገልገል የቻለው ይህ ተጫዋች በቀጣዩ ክረምት ወደ እንግሊዝ እንደሚመለስ ቢጠበቅም እርሱ ግን የተወለደባትን ሀገር የኢትዮጵያን መለያ የመልበስ ፍላጎቱ ከፍ ያለ እንደሆነ ይናገራል።
አስተያየት ይስጡ