አሁን ደግሞ በካናዳ ወጣት ቡድኖች ደምቆ ኢትዮጵያን እየናፈቀ ያለው ወጣቱ ግብ ጠባቂን እናስተዋውቆ።
ከዛሬ አስራ ስምንት አመት በፊት ከሆላንዳዊቷ እናቱ እና ከኢትዮጵያዊው አባቱ በካናዳ ቶሮንቶ ኦናታሪዮ ውስጥ ለመወለድ የበቃው 1 ሜትር ከ85 ሴንቲ ሜትር የሚረዝመው ናታንኤል አብርሀም በትምህርቱ ጎበዝ ከመሆን ባለፈ እግር ኳስን ጎን ለጎን መጫወት የጀመረው ገና የአካዳሚ ተማሪ እያለ ነበር።

እግር ኳስን አጥብቆ የሚወደው እና ዕረፍቱንም ባስኬት ቦል ፣ ዋና እና ፊልምን መመልከት የሚያስደስተው የ18 አመቱ ወጣት ግብ ጠባቂ ካናዳ በሚገኘው እና በተማረበት ቢል ክሩዘል ሀይስኩል ውስጥ በ11 አመቱ ምርጥ ግብ ጠባቂ በመሸለሙ በፍጥነት ወደ ቶርንቶ የእግር ኳስ ማሰልጠኛ በመግባት ራሱን እያበቃ ለተወለደባት ካናዳ በአለም እና በሰሜን አሜሪካ የኮንካ ካፋ ማጣሪያዎች እና ውድድሮች ከ17 ከ18 እና ከ20 አመት በታች ብሔራዊ ቡድኖቿን ወክሎ በመጫወት ጥሩ ጊዜን አሳልፏል።
በአሁኑ ሰዓት በካናዳው ፉትቦል ሰብ ዲቪዢን እየተባለ በሚጠራው ሊግ ውስጥ በሚሳተፈው ሊዊስፍል ካርዲል ወይም ዩኒቨርስቲ ኦፍ ሊዊስፍል ክለብ ውስጥ እየተጫወተ ያለው በክረምቱም ወደ አሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር እንደሚያመራ ስሙ እየተነሳ ያለው ግብ ጠባቂው በቅርቡ በዋናው የካናዳ ብሔራዊ ቡድን የመጠራት ዕድሎች እንዳሉት የሰማሁ ሲሆን እርሱ ግን የኢትዮጵያን ታሪክ ከሰማ በኋላ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን መለያ ለብሶ ለማገልገል ዝግጁ ነኝ ሲል ገልጿል።
አስተያየት ይስጡ