መነሻ ገጽ ኢትዮጵያን በውጪ የኢትዮጵያን መለያ የመልበስ ፍላጎት ያለው በኖርዌይ የተወለደው ግብ ጠባቂ
ኢትዮጵያን በውጪዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

የኢትዮጵያን መለያ የመልበስ ፍላጎት ያለው በኖርዌይ የተወለደው ግብ ጠባቂ

አጋራ
አጋራ

ዋልያዎቹን ለማገልገል ትልቅ ህልም ያለው ቁመታሙ ግብ ጠባቂ ማነው ?

ስሙ ዳንኤል ንጉሴ ስክሬትበርግ ይባላል ተወልዶ ያደገው በኖርዌይ ሲሆን በእናቱ ኢትዮጵያዊ በአባቱ ደግሞ የኖርዌይ ዜግነት ያለው 1 ሜትር ከ90 ሴንቲ ሜትር የሚረዝም ቁመታም የግብ ዘብ ነው። እግር ኳስን በኖርዌይ ስትሮምስ ጎድ ሴት በተባለው ቡድን የልጅነት ዕድሜውን ያሳለፈ ሲሆን ለዚህም ክለብ በሁለት አጋጣሚ ተመላልሶ ግልጋሎትን ሰጥቷል።

አሮቮል ፣ ቤሩም ፣ ኦርን ኦርተል እና አሲደን በተባሉ ሌሎች የትውልድ ሀገሩ ኖሮዌይ ክለቦች ውስጥ ጥሩ ጊዜ የነበረው ይህ የ24 አመቱ ግብ ጠባቂ ወደ ፊላንድ በማምራትም ሙሳ እና ሚክ ኬሊን በተባሉ የሊግ ክለቦች ውስጥ መጫወት የቻለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓትም ወደ ሀገሩ ኖርዌይ በመመለስ ከፍ ባለ የገንዘብ ዝውውር ኦቦስ ሊጋን እየተባለ በሚጠራው የሀገሪቱ ሁለተኛ ዲቪዚዮኑ ተካፋዩ ስትሮም ሜን ክለብ እየተጫወተ ይገኛል።

ለኖርዌይ ከ15 አመት በታች ብሔራዊ ቡድን የተጫወተው እና በአሰልጣኝ ዳንኤል ገብረማርያም ከሦስት አመት በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ከደቡብ አሜሪካዊቷ በሰሜን አትላንቲክ ከምትገኘዋ ጉያና ጋር ተጫውቶ በሽመልስ በቀለ ጎሎች 2ለ0 ስናሸነፍ በቡድኑ ለመጠራት የበቃው ግብ ጠባቂ ለዘመናዊ እግር ኳስ ምቹ እና በእግር በመጫወት ከፍ ያለ ብቃት ቢኖረውም ኢትዮጵያን የማገልገል ውጥን ቢኖረውም ይህ ቁመታም ግብ ጠባቂ ግን ህልሙ እና ኢትዮጵያ ሊገናኙለት አልቻሉም ይህ የግብ ዘብ ለኖርዌይ ዋናው ብሔራዊ ቡድን ከመጫወት ይልቅ የእናቴን ሀገር ለማገልገል ዝግጁ ነኝ ሲል አሳውቆኛል።

አጋራ

አስተያየት ይስጡ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

ተዛማጅ ጽሑፎች
ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ሀድያ ሆሳዕና ፣ ፋሲል ከነማ እና ወላይታ ድቻ ወሳኝ ድል አግኝተዋል

በሊጉ የሳምንቱ የሁለተኛ ቀን መርሀግብር ሀዋሳ ከተማ ወደ ሊጉ መሪ የሚጠጋበትን ዕድል...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየጨዋታ ዘገባ

ፈረሰኞቹ በድል ሲቀጥሉ ንግድ ባንክ እና ድሬዳዋም አሸንፈዋል

ቅዱስ ጊዮርጊስ ተከታታይ ድሉን ወደ ቋቱ ሲከት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከጨዋታ ብልጫ...

ዋልያዎቹዜናዎችየኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን

አንጋፋው አሰልጣኝ በስማቸው የእግር ኳስ ማሰልጠኛ አካዳሚ ሊገነባላቸው ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር ሰውነት ቢሻውን ለማመስገን እና ዕውቅና ለመስጠት...

ዜናዎችየኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግየዲሲፕሊን ውሳኔዎችዲሲፕሊን ውሳኔ

የዲሲፕሊን ውሳኔዎች

1. ፉአድ ኢብራሂም (ኢትዮጵያ ቡና) : ከታች በተጠቀሱት 5 ጨዋታዎች የቢጫ ማስጠንቅቂያ...